የጋህአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በጋምቤላ ከተማ ስብሰባ ጀምሯል

110

ጋምቤላ ሚያዝያ 22/2011 የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋህአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡

የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ስብሰባው ሲጀመር እንዳሉት ስብሰባው በክልሉ ወቅታዊ   ጉዳዮች ላይ ለመወያየት የተጠራ ነው።

በዚህም በወቅታዊ የሰላም፣ የፀጥታና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ በስፋት ይመክራል ብለዋል።

ድርጅቱ በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቀረበው ሰነድ ላይ በመወያየት ውሳኔ እንደሚያስተላልፍም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም