በለንደን ማራቶን በወንዶች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀቁ።

59

አዲስ አበባ ሚያዝያ 20/2011 ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በለንደንማራቶን ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

በለንደን ማራቶች  የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነው ኬኒያዊው ኤሊውድ ኪፕቾጌ 2 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ  በአንደኝነት አጠናቋል።

ኢትዮጵያዊያኑ ሞስነት ገረመው 2 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ55 ሴኮንድ ሁለተኛ፣ አትሌት ሙሌ ዋስሁን በ2 ሰዓት ከ3 ደቂቃ 16 ሴኮንድ  ሶስተኛ ደረጃን ሲይዙ አትሌት ቶላ ሹሬ ደግሞ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በውድድሩ ከኢሊድ ኪችቾጌ  ቀጥሎ ተጠብቆ የነበረው እንግሊዛዊው ሙሐመድ  ፋራህ (ሞፋራህ) 5ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

በተመሳሳይ በሴቶች የተደረገውን ውድድር ኬንያዊቷ ብርጊድ ኮሴጊያ በ2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆናለች።

ሌላኛዋ ኬኒያዊት ቪቪያን ቼሮይት በ2 ሰዓት 20 ደቂቃ  ከ14 ሴኮንድ ሁለተኛ ስትወጣ ኢትዮጵያዊቷ ሮዛ ደረጀ ደግሞ በ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ51 ሴኮንድ ሶስትኛ በመሆን ውድድሯን አጠናቃለች።

ባለፈው ዓመትም በዚሁ ውድድር የዛሬው አሸናፊ  ኬኒያዊው ኢሊውድ ኪፕቾጌ አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ እንሊዛዊው ሞ ፋራህ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ነበር ያጠናቀቀው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም