የጋምቤላ ክልል በዶክተር ነጋሶ ሞት ኀዘኑን ገለጸ

64

ሚያዝያ  19/2011  የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ኅልፈተ ህይወት የተሰማውን ኅዘን ገለጸ።

የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ኅልፈተ ህይወት የተሰማውን ኅዘን ገለጸ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቀው በቀድሞው በቀድሞው ርዕሰ ብሔር ህልፈተ ህይወት የክልሉ መንግሥትና ህዝብ ጥልቅ ኅዘን ተሰምቷቸዋል።

ዶክተር ነጋሶ  ከወጣትነት ጊዜያቸው ጀምሮ ለአገራቸውና ለህዝባቸው እንደታገሉ አመልክቷል።

''ዶክተር ነጋሶ ርዕሰ ብሔር ሆነው ባገለገሉበት  ጊዜም፣ ደከመኝ ሰለቼኝ ሳይሉ ለአገራቸውና ለህዝባቸው በርካታ ተግባራትን ያከናወኑ ታላቅ ሰው ነበሩ '' ብሏል።

በኢትዮጵያ ሰፊና ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ምህዳር እንዲፈጠር ድርሻ ማበርከታቸውን አስታውቀዋል።

ጽህፈት ቤቱ ለዶክተር ነጋሶ ቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶችና ለኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ተመኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም