የቤልት ኤንድሮድ ኢኒሼቲቭ ለአለም ኢኮኖሚ እድገት መፋጠን ከፍተኛ አስተዋፅዎ አድርጓል-ፕሬዝዳንት ሺ

67

ሚያዝያ 19/2011 የቻይናውፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በ2ኛው የቤልት ኤንድሮድ ኢኒሼቲቭ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት ማዕቀፉ ለአለም ሀገራትኢኮኖሚያዊ እድገት መፋጠን አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሺ የዛሬ ሁለት አመት በተካሄደው ፎረም ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች ቀስበቀስ እየተተገበሩ መሆናቸውን ጠቅሰው ፤ለዚህ ስኬት የተባበሩ ሀገራት እና አለም አቀፍ ድርጅቶችን አመስግነዋል፡፡

እስካሁን ከ150 በላይ ሀገራት እና አለም አቀፍ ድርጅቶች የቤልት ኤንድሮድ ኢኒሼቲቭ ለአለም አቀፍ ትብብር ስምምነትን ከቻይና መንግስትጋር መፈራረማቸውን ፕሬዝዳንት ሺ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም በቤልት ኤንደሮድ ኢኒሼቲቭ ማዕቀፍ ስር ባሉ ሀገራት የዜጎች የኑሮ ደረጃ ተሻሽሏል ፤በርካታ የስራ አድሎች ተፈጥረዋል፤በሀገራቱ እና ቻይና የኢኮኖሚ እድገት ተመዝግቧል፡፡

የቤልት ኤንድሮድ ኢኒሼቲቭ አለምአቀፍ ትብብር በሀገራት መካከል የንግድ እና መሰረተልማት ትስስር የመፍጠር ግቡን እንደሚያሳካ ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ አረጋግጠዋል፡፡

በቤልት ኤንድሮድ ፎረም የምናደርገው ትስስር ሊተገበር የሚችል፤ግልጽ መርህን የሚመከተል፤ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ፤የዜጎችን የኑሮደረጃ የሚያሻሽል ፤ቀጣይነት ያለው እድገት የሚያስመዘግብ መሆን አለበት ነው ያሉት፡፡

ቻይና በሳይንስ ፤ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ መስክ ከተባባሪ የቤልት ኤንድሮድ ሀገራት ጋር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶቸን ለመደገፍ የድርጊት መርሀግብር በማዘጋጀት የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ትፈልጋለች ብለዋል፡፡

በዚህም በሚቀጥሉት 5 አመታት ከፎረሙ አባል ሀገራት ለተውጣጡ 5 ሺህ ሰዎች ሀገራቸው የልምድ ለውውጥ እና የስልጠና እድል እንደምትሰጥ ነው የጠቀሱት፡፡

የሀገራት ያልተመጣጠነ የኢኮኖሚ እድገት የወቅቱ የአለማችን ችግር ነውያሉት ፕሬዝዳንት ሺ፤ አዳጊ ሀገራት ድህነትን እንዲያስወግዱ እና ዘላቂ ልማት እንዲያስመዘግቡ እድሎችን መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ቻይና በግብርናው መስክ፣ በጤና፤ አደጋ መከላከል እና በውሃ ሀብት አጠባበቅ ዙሪያ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር ጭምር ጥልቅ ትብብሮችን እንደምታደርግ ፍንጭ ሰጥተዋለ፡፡

በመሰረተ ልማት መተሳሰር የቤልት ኤንድሮድ ዋነኛ ግብ ነውያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የመልከዓምድር እርቀትን በመገደብ ለጋራ እድገት እና ብልፅግና በአንድነት መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

በዚህ ፎረም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የ37 ሀገራት መሪዎች ፤የአለም አቀፍ ድርጅቶች እና ተወካዮች በመካፈል ላይ ይገኛሉ፡፡ ሁለተኛው የቤልት ኤንድሮድ ለአለም አቀፍ ትብብር ፎረም ለሶስት ቀናት የሚካሄድ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም