ቤተ እምነቶች ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታትየድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

57

የደቡብ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ትኩረት ከተሰጣቸው ዞኖች ከተሰበሰቡ የኃይማኖት አባቶች ጋር በሆሳ እና ከተማ ውይይት አድርጓል፡፡

በዚህ ወቅት የክልሉ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ፓስተር ተሰማ ታደሰ እንደተናገሩት በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ቤተ እምነቶች ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በማስቀረት ረገድ ጉልህ ሚና አላቸው፡፡

ቤተ እምነቶችና የኃይማኖት አባቶች ተሰሚነታቸዉ የጎላ በመሆኑ በተለይ ለችግሩ ሰለ የሚሆኑት ወጣቶችን ጉዳቱንና አስከፊነት ትኩረት ሰጥተው በማስተማር የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

ውይይት  ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን  ለመከላከል የሁሉም ቤተ እምነት አባቶች ኃላፊነትን ከተጠያቂነት ጋር የሚሰጥበት እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡ 

ከስልጤ ዞን የኃይማኖት ተቋማት ፎረም የተገኙት ሀጂ ኡስማን አብደላ በበኩላቸው ህገ ወጥ ጉዞን ለማስቀረት እንደ እስልምና ኃይማኖት እየተሰራ ቢሆንም የሚጠበቀው ያህል ለውጥ እንዳልመጣ ተናግረዋል፡፡

ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ያለውን አስከፊነት ታሳቢ በማድረግ የኃይማኖቱ አንድ ተግባር በማድረግ ለመስራት እንደተነሳሱም አስታውቀዋል፡፡

እንደ ኃይማኖት አባት ተከታዮቻቸውን በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተሳታፊ እንዳይሆኑ በማድረግ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ሀጂ ኡስማን ገልጸዋል፡፡

"ሀገር ልትለማ የምትችለው በህገ ወጥ ጉዞ የሚያልቁ ወጣቶችን ከህገ ወጥ ጉዞ መታደግ ስንችል ነው" ያሉት ደግሞ ከሀድያ ዞን የኃማኖት ተቋማት ፎረም የተሳተፉት ቄስ ፍሰሀ ወልደአማኑኤል ናቸው፡፡

በሀገር ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻልና ለውጥ በሀገር ውስጥ እንዳለ  ቤተ እምነቶችና የኃይማኖት አባቶች በማስተማር ወጣቶቹ ሀገራቸውንም ህዝባቸውንም እንዲጠቅሙ በማድረግ  የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

እንደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የኃይማኖት ተቋም የስራቸው አንድ አካል በማድረግ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማስቀረት  እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ለአንድ ቀን በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ከሰባት  ዞኖችና ከሀዋሳ ከተማ ከተጋበዙ የኃይማኖት አባቶች ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም