በኢትዮጵያ አራት የቻይና ኩባንያዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ሊሰማሩ ነው

1540

ሚያዝያ 18/2011 የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ከሚሰማሩ አራት የቻይና ኩባንያዎች ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።

ስምምነቱ የተደረገው በቻይና እየተካሄደ ካለው የቤልትና ሮድ ጉባኤ ጎን ለጎን እንደሆነ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ቴይሰንና ግሪን ዳይመንድ የተባለው ኩባንያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ በአመት እስከ 1 ሚሊዮን ቶን ወረቀት ከቀርከሃ የሚያመርት ፋብሪካ ነው።

አሚቲ ህትመት የተሰኘ ኩባንያም በኢትዮጵያ ማተሚያ ቤት ለመክፈት የሚያስችለውን ስምምነት ነው ያደረገው።

ሌላኛው ሲ.ጂ.ሲ.ኦ.ሲ የተሰኘ ቡድን በአመት እስከ 300 ሺህ ከብትና 3 ሚሊዮን በጎች ለገበያ የሚያቀርብ የቁም ከብትና ስጋ ማዘጋጃ ቄራ በአፋር ክልል ለመክፈት ተስማምቷል።

አራተኛው ዜንዴ የህክምና ውጤቶች ማምረቻ ሲሆን በቂሊንጦ የኢንዱስትሪ ፓርክ የቁስል ማከሚያ፣ የቀዶ ጥገና ማከናወኛና ሌሎች የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን ያመርታል።