የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አነሳ

72
አዲስ አበባ ግንቦት 28/2010 የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወሰነ። ምክር ቤቱ ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው አዋጅ እንዲነሳ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት በቀረበለት የውሳኔ ሃሳብ ላይ በስፋት ተወያይቷል። በዚህም መሰረት ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመጠበቅ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በስምንት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ እንዲሻር ወስኗል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 23 ቀን 2010 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው  አዋጁን ማፅደቁ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም