በጅማ ከተማ በእሳት ቃጠሎ ጉዳት ደረሰ

64
ጅማ ሚያዝያ  17/2011   በጅማ ከተማ   በተለምዶው ፈረጂ አራዳ በተባለው ሰፍራ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ፖሊስ አስታወቀ። በጅማ ከተማ   በተለምዶ  ፈረጂ አራዳ በተባለው ሰፍራ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ። የከተማው ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዚዮን ኃለፊ ኢንስፔክተር ገዛኸኝ አውግቻው እንደገለጹት የእሳት ቃጠሎ የተከሰተው ትናንት ማምሻውን   12 ሰዓት ተኩል አካባቢ ሜላት ከተባለ ሬስቶራንት  ነው፡፡ ቃጠሎው እንዳይስፋፋ ድጋፍ ሲያደረጉ በነበሩ ሶስት ሰዎች  ላይ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው በጅማ ሆስፒታልየ ህክምና ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። በቃጠሎው አምስት የንግድ ሱቆችና አንድ የመንግስት ደርጅት ሙሉ በመሉ ሲወድሙ 11 ቤቶችላይ  በከፊል ጉዳት መድረሱን ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የጅማ አባጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ የእሳት አደጋ መከላከያ፣ የጅማ ከተማ የእሳት  አደጋ መከላከያ፣ የጸጥታ አካላት እና የአካባቢው ነዋሪዎች ባደረጉት ርብረብ ቃጠሎው  ሳይስፋፋ መቆጣጠር መቻሉን አስረድተዋል፡፡ የእሳት ቃጠሎው መንስኤና ያደረሰው የንብረት ጉዳት መጠን  እየተጣራ እንደሚገኝ  ኢንስፔክተር ገዛኸኝ ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ ከበዓሉ ዝግጅት ጋር ተያይዞ መሰል አደጋ እንዳይፈጠር ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም