የአምቦ ማዕድን ውሃ ፋብሪካ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ የ200ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ

74
ሚያዝያ 16/2011 የአምቦ ማዕድን ውሃ ፋብሪካ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለችግረኞች 200ሺህ ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ። የአምቦ ማዕድን ውሃ ፋብሪካ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለችግረኞች ከ200ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አደረገ። ፋብሪካው  200 ለሚሆኑ ለችግረኛ ቤተሰቦችና ሕጻናት የለገሰው ብርድ ልብሶች፣አልባሳትና አንሶላዎችን ነው። የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ መኮንን በዚሁ ወቅት  እንደተናገሩት ድጋፉ የተደገረገው ችግረኞቹ በዓሉን እንደ ማንኛውም ሰው ተደስተው እንዲያሳልፉ ታስቦ ነው፡፡ ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል ወይዘሮ አበበች መርጋ በሰጡት አስተያየት በቀን ሥራ  በሚያገኙት አነስተኛ ገቢ  ኑሮአቸውን ለመምራት ይቸገሩ እንደነበር ገልጸው፣በድርጅቱ የተሰጣቸው አንሶላና ብርድ ልብስ ችግራቸውን እንደሚያቃልላቸው ገልጸዋል። የአምቦ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተረፈ በዳዳ ፋብሪካው ለችግረኛ ወገኖች ላደረገው ድጋፍ አመስግነው፣ሌሎችም ድርጅቶች አርአያነቱን  እንዲከተሉ ጠይቀዋል ። ትንሳዔ ሕዝበ ክርስቲያን በመረዳዳትና በመደጋገፍ የሚያከብረው በዓል መሆኑ ይታወቃል። የዚህ ዓመት የትንሳዔ በዓል የፊታችን እሁድ ይከበራል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም