አሜሪካ የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣኑን ካላስረከበ  ማዕቀቡን እንደማታነሳ አስታወቀች

57
ሚያዚያ 16/2011 አሜሪካ የወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳደር ካላስተላለፈ በሀገሪቱ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ እንደማታነሳ አስታወቀች። የአሜሪካ ለአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ማኪላ  ጀምስ በሱዳን ላይ የተጣለው ማዕቀብ የሚነሳው ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ስልጣኑን ሲያስረክብ ነው ብለዋል። ሚኒስትር ዴኤታዋ ከሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሌተናል ጀኔራል አብደል ፋታህ አብደልራህማን ቡርሃን ጋር ተወያይተዋል። ጀኔራሉ  የህዝቡን ሲቪል አስተዳደር ፍላጎት ምላሽ እንዲያገኝ ፅኑ እምነት ያላቸው መሆኑን እንደገለጹላት ሚስ ማኪላ ተናግራለች። ምንጭ፦ቢቢሲ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም