የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሩሲያ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሩሲያ ገቡ
90
ሚያዚያ 16/2011 የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ለመወያየት ሩሲያ ገቡ። ኪም ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመወያየት ነው በልዩ ባቡራቸው ከፒዮንግያንግ ተነስተው ሩሲያ የገቡት። የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሲገናኙ ይህ የመጀመሪያቸው ነው ተብሏል።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ሃሳን የባቡር ጣቢያ ሲደርሱ በሩሲያ የሩቅ ምስራቅና የአርክቲክ ሚኒስትሩ አሌክሳንደር ኮዝሎቭና ሌሎችም ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል። በስፍራው ሲደረሱም “የኪም ኢል ሱንግ ቤት” እየተባለ የሚጠራውን የሩሲያና የኮሪያ ወዳጅነት ቤት መጎብኘታቸው ተሰምቷል። በአሁኑ ወቅት ከፑቲን ጋር ወደሚገናኙባት ቭላዲቮስቶክ ከተማ በባቡራቸው እየተጓዙ ነው ተብሏል። ኪም ከከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ወደ ሩሲያ ማቅናታቸውን የሰሜን ኮሪያ ማዕከላዊ ዜና ኤጀንሲ አስታውቋል። ኪምና ፑቲን ነገ በሩሲያ የፓሲፊክ ወደብ ከተማ ቭላዲቮስቶክ የሚገናኙ ሲሆን በፒዮንግያንግ የኒዩክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ የክሬምሊን ባለስልጣናት ጠቁመዋል። ምንጭ፦ www.aljazeera.com/ TASS Russian News Agency