መቐሌ 70 እንደርታ አዳማ ከነማን አሸነፈ

78
መቐለሚያዝያ 13/2011 በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ 21ኛ ሳምንት ውድድር መቐሌ 70 እንደርታ ክለብ አዳማ ከነማን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል። ክለቡ መሪነቱን ያጎለተበትን ውጤት ያገኘው ዛሬ በመቐለ ትግራይ አለም አቀፍ ስታዲዬም ተጋጣሚውን ሁለት ለአንድ በመርታቱ ነው። ለክለቡ ኮከብ ተጫዋቹ  አማኑኤል ገብረሚካኤል በ35ኛው  እንዲሁም ያሬድ ከበደ በ67ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠሯቸው ግቦች ነው። በዚህም መቐሌ 70 እንደርታ በሊጉ የሰበሳባቸውን ነጥቦች  ከ42 ነጥብ ወደ 45 ነጥብ ከፍ አድርጓል። አዳማ ከነማ ክለብ ተጫዋች አቡበከር ነስሩ ባስቆጠራት ግብ  በባዶ ከመውጣት የሚያስችለውን ግብ አስቆጥሯል።ክለቡ 26 ነጥብ አለው። ጨዋታውን 60 ሺህ የሚደርስ የመቐለ ከተማና አካባቢ ደጋፊዎች ጨዋነት የተሞላበት ድጋፍ ሰጥተዋል።የከተማው ሕዝብና  የስፖርት ደጋፊዎች ማህበር ለአዳማ ከነማ ክለብ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ 19 ኪሎ ሜትር ድረስ በመሄድ አቀባበል አድርገውለታል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም