የኦሮሚያና አማራ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ መድረክ ተሳታፊዎች አምቦ ከተማ ገቡ

321

ሚያዝያ 12/2011 በነገው እለት የሚካሄደው መድረክ የፌዴራል እና የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ የአመራር አባላት ይሳተፋሉ ተብሎም ይጠበቃል።

መድረኩ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ይበልጥ በማጠናከር ለአገራዊ አንድነትንና የተጀመረውን ለውጥ  ለማሳለጥ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም በጥቅምት ወር 2010 ዓ.ም በቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ  መገርሳ የተመራ የልዑካን ቡድን በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ተገኝቶ ተመሳሳይ መድረክ ማካሄዱ ይተወሳል።

በወቅቱ የተካሄደው መድረክ በአማራና በኦሮሞ ሕዝቦች መካከል ለዘመናት የዘለቀውን የመደጋገፍ፣  የመተጋገዝና አብሮነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመም ነበር።

አሁንም ተመሳሳይ ዓላማ ያለው የህዝብ ለህዝብ መድርክ በነገው እለት በአምቦ የሚካሄድ ይካሄዳል።