በሮቤ በ187 ሚሊዮን ብር አውቶብስ መናኸሪያ ሊገነባ ነው

52

ጎባ ሚያዝያ 11/ 2011 የትራንስፖርት መሰረተ ልማትን በማስፋፋት አገልግሎቱን ቀልጠፋ ለማድግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ገለጸ፡፡

በባሌ ሮቤ ከተማ ከ187 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ለሚገነባው አዲስ ዘመናዊ መናኸሪያ የመሰረት ድንጋይ ዛሬ ተቀምጧል፡፡

የመሰረት ድንጋዩን ያኖሩት የክልሉ የትራንስፖርት ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ አህመድ አባጊሳ እንደተናገሩት የክልሉ መንግስት የትራንስፖርት አገልግሎትን ቀልጠፋ ለማድረግ በመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ አትኩሮ እየሰራ ነው፡፡

መናኸሪያውን በተሻለ መንገድ አገልግሎት እንዲሰጥ በኮንክሪት አስፋልት ደረጃ እንደሚገነባ የተናገሩት ምክትል ዳይሬክተሩ ለተለያዩ የቢሮና ተያያዥ አገልግሎቶች የሚውል ባለ ሁለትደረጃ ፎቅ ሕንጻን ያከተታ መሆኑንም ገልጿል፡፡

ሶስት ሄክታር በሚጠጋ መሬት ላይ የሚሰራው ዘመናዊ መናኸሪያው በቀን ከ1ሺህ 200የሚበልጡ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም እንዳለውም ተናግረዋል፡፡

አዲስ የሚገነባው መናኸሪያ የትራስንፖርት አገልግሎትን ከማሳለጡም በላይ የአካባቢውንየቱሪዝም ፍሰት በማሳደግ ረገድ ድርሻው ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የክልሉ መንግስት በመደበው በጀት የሚሰራው ይህ መናኸሪያ ሶስት ሔክታር በሚጠጋ መሬት ላይ የሚገነባ ሲሆን በ540 ቀናት ውስጥ እንዲጠናቀቅም ታስቧል።

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ብርሃኑ ዳዲ በበኩላቸው እንደገለጹት በከተማው የሚገኘውነባሩ መናኸሪያ  ለበርካታ ጊዜያት ከፍተኛ የህዝብ ቅሬታ ሲነሳበት መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

አዲሱ መነሃሪያ ለህዝብ ምላሽ ከመስጠትና የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር ከመቅረፍምበተጓዳኝ የነዋሪዎችን የስራ እንቅስቃሴ የነቃቃል የሚል እምነት እንዳለቸው ገልጸው ፕሮጄክቱበወቅቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የሚፈለግባቸውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉተናግረዋል፡፡

ከከተማዋ ነዋሪዎቹ መካከል አቶ አህመድ አማን በሰጡት አስተያየት ግንባታው የሚበረታታመሆኑን ገልጸው የአካባቢውን ህዝብ ቅሬታ ለመፍታት ታስቦ የሚቀመጥ የመሰረት ድንጋይ በወቅቱ ግንባታው ሊከናወን ይገባል።

ከከተማዋ አሽከርካሪዎች መካከል አቶ አሸናፊ መንግስቱ በበኩላቸው ነባሩ መናኸሪያከሚያስተነግደው የተሽከርካሪ ብዛትና  ከሰጠው ረጅም አገልግሎት የተነሳ በበጋ አቧራና በክረምት ደግሞ ውሃ እየሞላ ተገልጋዮችን ሲያንገላታ መቆየቱን ተናግረዋል።

አዲሱ መናኽሪያ በአስፋልት ኮንክሪት የሚገነባ መሆኑ የተቀላጠፈ የትራንስፖርት አገልግሎት ለተጠቃሚው ከመስጠት በተጓዳኝ ለእቃ መለዋዋጫ በየጊዜው ያወጡ የነበረውን ወጪእንደሚያስቀርላቸውም ገልጸዋል።

ባለሥልጣኑ የሚሰጠውን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማቀላጠፍ የባሌ ሮቤን ጨምሮ በአምስትየክልሉ ከተሞች ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ አዳዲስ ዘመናዊ መናኸያዎችን ለመገንባት በትኩረት እየሰራ መሆኑንን ከክልሉ ትራንስፖርት ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም