ኢትዮጵያ 'የዋን ቤልት ዋን ሮድ ኢንሼቲቭ' መሳካት ጉልህ ሚና አላት - በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጂያን

71

ሚያዝያ 8/2011 በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጂያንበቻይና መንግስት የሚተገበረውንና በርካታ አገሮችን የሚያገናኘው የዋን ቤልት ዋን ሮድ ኢንሼቲቭ ሁለተኛ ጉባዔ በቻይና ቤጂንግ እንደሚካሄድ መግለጫ ሰጠተዋል።

አምባሳደር ጂያን እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ካላት ጉልህ የዲፕሎማሲ ተሳትፎና የኢኮኖሚ መሻሻል አኳያ ለፕሮጀክቱ መሳካት ጉልህ ሚና አላት።

ኢትዮጵያ ኢንሼቲቩን በቀዳሚነት ከፈረሙት አገሮች አንዷ ስትሆን፤ ለዚህም ጠንካራ ተሳትፎ እያደረገች መሆኑንም አመልክተዋል።

በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄደው ስብሰባም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጉባዔው ላይ ከ124 በላይ አገሮች ልኡካንና ከ40 በላይ የአገር መሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ በተጨማሪም በአፍሪካና በሌሎች አህጉራት በፍጥነት እያደገ የመጣው የኢንዱስትሪ ግንባታና አለም አቀፋዊነት መርህ ሌላው ጥሩ አጋጣሚ ሲሆን፤"ኢንሼቲቩ ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር ሌላ ፖለቲካዊ አላማ የለውም"  ሲሉም አምባሳደሩ አስረድተዋል።

ለዚህም የዋን ቤልት ዋን ሮድ ኢንሼቲቭ  ከተባበሩት መንግስታት፣ከአፍሪካ ህብረትና ከሌሎች ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ የልማት ፕላኖች ጋር ተጣጥሞ እየሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

የዋን ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭይፋየተደረገውበፕሬዝዳንት ሺ ዢፒንግ በአውሮፓዊያኑ 2013 ሲሆን፤ ሀሳቡ ያተኮረው የህዝብ ለህዝብ ልውውጥ፣ የጋራ ተጠቃሚነት እና ተሳታፊ አገሮች ጥቅምን እንዲጋሩ በማድረግ ላይ ነው ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም