የደቡብ ወሎ ዞን አርሶ አደሮች በኅብረተሰቡ ጉልበት የተከናወኑ የተፋፈስ ልማት ሥራዎች ተጠቃሚ አድርገውናል አሉ

150

ደሴ ሚያዝያ 10 ቀ/ 2011 በኅብረተሰቡ ተሳትፎ የተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች  በእርሻ  ሥራቸው እንዳገዟቸው የደቡብ ወሎ ዞን አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡

በዞኑ በበጋ ወቅት ከ40 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተፋሰስ ሥራዎች  ተሸፍኗል፡፡

ከዞኑ አርሶ አደሮች አንዳንዶቹ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳመለከቱት በዞኑ በየዓመቱ የሚከናወኑት የተፋሰስ ልማት ተግባራት ምርታማነትን ለማሳደግ ረድቷቸዋል።

በደሴ ዙሪያ ወረዳ የ010 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አወል አህመድ ሥራዎቹ  ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዳበቋቸው ይናገራሉ።

በዚሀምየእርሻመሬታቸውየአፈር ለምነት ከማሻሻሉም በሄክታር ከ15 ኩንታል በታች ከሚያገኙበት ሰብል ከሚያገኙበት ማሳ  ከ25 ኩንታል  በላይ ምርት  ማግኘታቸዉን ገልጸዋል፡፡

ዘንድሮም በማሳቸዉ ላይ በተሰራላቸዉ የእርጥበት ማቆያ ዘዴ በግማሽ ሄክታር መሬት ላይ ገብስ መዝራታቸዉን አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁምበተራራማ ቦታዎች በሚሰራዉ እርከንና ክትር ለእንሰሳት መኖ የሚሆኑ ችግኝ፣ ሳርና ጓሳ በመትከል ለእንስሳት ቀለብ ማዋላቸዉን ተናግረዋል፡፡

ሌላዉ አርሶ አደር ይመር ሁሴንየአፈሩ ለምነት በመጠበቁ 15 ኩንታል ገብስ ከሚያገኝበት ማሳ እስከ 25 ኩንታል በማግኘት ምርታማነታቸው ማደጉን አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም አትክልትና ፍራፍሬ በማልማት  በዓመት እስከ 15 ሺህ ብር ተጨማሪ ገቢ እያገኙሁ ነው ብለዋል፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የተፈጥሮ ሀብት ቡድን መሪ አቶ መገርሳ ተሾመ በበኩላቸው በዞኑ የተከናወኑ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ለአርሶ አደሩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እያስገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በበጋ ወቅት 40 ሺህ 200 ሄክታር መሬት ላይ የተፋሰስ ሥራዎች መከናወናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ከአንድ ሺህ በላይ በሚቢልጡ ተፋሰሶች ውስጥ በተከናወነው ሥራም ከ428 ሺህ በላይ ሕዝብ መሳተፉን ተናግረዋል፡፡

በልማት ስራው 736 የእጅ ጉድጓዶች፣ኩሬዎችና ምንጮች መጎልበታቸውንም  አስረድተዋል።

በዞኑ ባለፉት ዓመታት ኅብረተሰቡን በማሳተፍ በ2 ሺህ 300 ተፋሰሶች ውስጥ 600 ሺህ ሄክታር መሬት የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ሥራዎች መከናወናቸውን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ይገልጻል፡፡