የህግ የበላይነት የማስከበር ስራዎች ላይ የምናደርገውን ክትትልና ቁጥጥር ለማጠናከር እንሰራለን- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

55

ሚያዝያ 10/2011 አስፈጻሚ አካላት የህግ የበላይነት ለማስከበር በሚያከናውኗቸው ስራዎች ላይ የሚያደርጉትን ክትትልና ቁጥጥር ለማጠናከር እንደሚሰሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለፁ።

አስፈጻሚ አካላት የህግ የበላይነት ለማስከበር በሚያከናውኗቸው ስራዎች ላይ የሚያደርጉትን ክትትልና ቁጥጥር ለማጠናከር እንደሚሰሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለፁ።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ የገለጹ  የምክር ቤት አባላት እንደተናገሩት በአገሪቱ የህግ የበላይነት በማስከበር ስራው ላይ የመዘግየትና በበቂ መጠን ያለመሰራት ችግሮች ይታያሉ።

ምክር ቤቱ አስፈጻሚ አካላት ላይ በሚያደርገው ክትትል ቀደም ሲል የነበረውን አካሄድ

በማሻሻል የቁጥጥርና ክትትል ስራውን ለማጠናከር እየሰራ ነው።

በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች በሚፈጠሩበት ወቅት ከአስፈጻሚ አካላት ጋር 

በመወያየት በድርጊቶቹ ላይ የሚሳተፉ አካላት ላይም እርምጃ እንዲወሰድና ተጠያቂ አካላትን የመለየት ስራዎች እንዲሰሩ እየተንቀሳቀስን ነው ያሉት።

ኮሚቴዎችን በማቋቋምም ግጭቶች በተፈጠሩባቸው አካባቢዎች የመስክ ምልከታ  የማድረግ፣ ህብረተሰቡን የማወያያት ንቃተ ህሊና የማሳደግና ከጽንፈኝነትና ወደ ግጭት ሊያመሩ ከሚችሉ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ የማስተማር ስራ እየሰራን ነው ብለዋል።

የህግ የበላይነት ማስከበር ካልተቻለ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መኖር ትርጉም የለውም  ሲሉም ተናግረዋል።

በአገሪቷ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ረብሻና ሁከት የሚፈጥሩ አካላት ላይ እርምጃ በመውሰድ በኩል መንግስት በትዕግስት መጠበቁን ገልጸው  ከዚህ በኋላ ግን በትዕግስት ማየት ሳይሆን ወደ ህግና ስርዓት ማስገባት ያስፈልጋል ብለዋል።

አቶ ቶመሬ የረሬ  በበኩላቸው በአገሪቱ ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮች ለመፍታት ያልተቻለው በአመራሮች በኩል የተለያዩ የቁርጠኝነት፣ የመዘግየትና ሌሎች ክፍተቶች መኖራቸው ሳቢያ መሆኑን ተናግረዋል።

ምክር ቤቱም ከአስፈጻሚ አካላት ጋር  የመስራትና ተጠያቂ በማድረጉ በኩል ወደ ተሻለ ደረጃ መሸጋገሩንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም