የአማራና የቅማንት ህዝቦችን አብሮነት ለማጠናከር የሚያስችል የዕርቀ ሰላም ኮንፈረንስ ተጀመረ

60

ሚያዝያ 10/2011 የአማራና የቅማንት ህዝቦችን አብሮነት ለማጠናከር የሚያስችል የዕርቀ ሰላም ኮንፈረንስ ዛሬ በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ ተጀመረ።

በዕርቀ ሰላም ኮንፈረንሱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር አምባቸው መኮንን ጨምሮ የክልል፣ የዞን የፌደራልና በመከላከያ ሠራዊት የ33ኛ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ከሁለቱም ብሔረሰብ ሕዝቦች የተውጣጡ ከ400 በላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችም እየተሳፉ ነው።

በሁለቱም ብሔረሰቦች መካከል እርቀ ሰላም በማውረድ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው ተመልሰው በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ማድረግ የኮንፈረንሱ ዓላማ መሆኑ በመድረኩ ተመልክቷል።

ቀደም ሲል በሁለቱ ብሔረሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ከቤት ንብተራቸው ተፈናቅለው በመጠለያ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም