ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ተጀመረ

63
ግንቦት 27/2010 ብሔራዊ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተናው በመላ ሀገሪቱ መጀመሩን  ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ። የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዘሪሁን ዱሬሳ በተለይ ለኢዜአ እንደተናገሩት ፈተናው በ993 ጣቢያዎች እየተሰጠ ነው። ተፈታኞች በዛሬው ዕለት የእንግሊዝኛ እና የሂሳብ ፈተናዎችን የሚወስዱ ሲሆን 284 ሺህ 312 ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸውን ዶክተር ዘሪሁን ተናግረዋል። እስከመጪው ሀሙስ ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም የሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም