ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢቫንካ ትራንፕን አነጋገሩ

83

አዲስ አበባ ሚያዝያ 07 2011ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከፍተኛ አማካሪ ኢቫንካ ትራንፕን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ከጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ጠቅላይ ሚነስትሩና አቫንካ ትራንፕ በቆይታቸው በዋናነት በሁለቱ አገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

 ኢቫንካ ትራንፕ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ከሴቶች እኩልነትና ተጠቃሚነት ጋር በተያያዘ ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር 

መክረዋል።

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉትን ተግባራት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን በዚህ ወቅት መናገራቸው ይታወሳል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልጅና አማካሪ ኢቫንካ ትራንፕ  ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለመሰል ጉብኝት ወደ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ኮትዲቯር ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም