ድሬዳዋ ከነማ ደደቢትን 3 ለ 2 አሸነፈ

68

መቀሌ ሚያዝያ 6/2011 በመቀሌ ትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ዛሬ በተካሄደ 20ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ድሬዳዋ ከነማ ደደቢትን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

ዛሬ በተካሄደውን ጨዋታ ድሬዳዋ ከነማ ሊያሸንፈ የቻለው ዘነበ ታደሰ በ16ኛው፣ ረመንዲ ያሲን በ44ኛው፣ ፌሬድ ምሸንዶ በ87ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠሩት ግብ ነው።

የድሬዳዋ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ዛሬ በማሸነፉ ደረጃውን ከ12 ወደ 10ኛ ማሻሻል ችሏል።

ለደደቢት እግር ኳስ ክለብ ያብስራት ተስፋይ በ58ኛው፣ መድሃኒየ ታደሰ በ90ኛው ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥረዋል።

ኢዜአ ያነጋገራቸው የድሬዳዋ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ ስምዖን አባይ የስፖርት ደጋፊዎች በጨዋነታቸው ሊቀጥሉበት እንደሚገባ አመልክተው "ጸጥታ አስከባሪዎች በአርአያነት የሚጠቀስ ስራ በመስራታቸው ኮርተንባችዋ" ሲሉ ተናግርል።

አሰልጣኙ ስለ ዳኞች ያለቸውን ደካማና ጠንካራ ጎን ከመግለጽ ታቅበዋል።

የደደቢት ዋና አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐየ በበኩላቸው "በፊት የነበረው የአሰልጣኝ፣ የተጫዋቾችና የበጀት ችግሮች አሁን ዋጋ እያስከፈሉን እንደሆነ ተረድተናል" ብሏል።

"ቡድኑ ካለበት 16ኛ ደረጃ ወደ 10ኛ ደረጃ ለመምጣት እንሰራለን፤ ህዝቡና መንግስትም የገንዘብ ድጋፉ ሊያደርጉልን ይገባል" በማለት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም