በፕሪሜየር እና ከፍተኛ ሊጎች ጨዋታዎች ወልዋሎ እና ሶዶ ከተማ አሸነፉ

64

መቀሌ/ሶዶ 5/2011 በዛሬው የፕሪሜየር እና  ከፍተኛ ሊጎች  የእግር ኳስ ጨዋታዎች ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ  እና ሶዶ ከተማ  ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ፡፡

በመቀሌ ትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲዬም በተካሄደው 20ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ መከላከያን አስተናግዶ አንድ ለባዶ ረትቷል።

ለወልዋሎ ጎሉን ያስቆጠረው  በ19ኛው ደቂቃ ላይ ነው፡፡

ከጨዋታው በኋላ  የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተጨዋች አፈወርቅ ኃይሉ በሰጠው አስተያየት  ከዚህ በላይ ግብ የምናስቆጥርበት ዕድል እያለን አልተጠቀምንበትም "ብሏል።

ጨዋታው ግን ፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት እንደነበር ተናግሯል።

የመከላኪያ ተጨዋች ዳዊት እስጢፋናስ በበኩሉ በጨዋታው ጥሩ ተሳትፎ ማድረጋቸውንና ደጋፊዎች መልካም ስነ ምግባር እንዳሳያቸው ገልጸዋል፡፡

ካደረጉት ጨዋታ ጉድለታቸውን ለይተው በማስተካከል በቀጣይ  ለተሻለ ውጤት እንደሚሰሩ አመልክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የ14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ የወንዶች ከፍተኛ ሊግ ውድድር ሶዶ ከተማ  በሜዳው የወልቂጤ ከተማ አቻውን አስተናግዶ ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸንፏል፡

ሶዶ ከተማ አሸናፊ የሆነባቸውን ግቦችን በ2ተኛውና  በ75ኛው ደቂቃ ላይ እንዲሁም በ73ኛው ደቂቃ ላይ ከሽንፈት ያልታደገቻቸውን ግብ የወልቂጤ ከተማ አስቆጥሯል፡፡

ለሶዶ ከተማ የመጀመሪያን ጎል የስቆጠረው  በረከት ወንድሙ ሲሆን ሁለተኛውን ደግሞ ጥላሁን በቶ ነው፡፡

ለወልቂጤ ከነማ ጎል ያስቆጠረው  አህመድ ሁሴን መሆኑ ታውቋል፡፡

የሶዶ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ሃብተማሪያም ጳውሎስ ያለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን መሸነፋቸውን አስታዉሰው በተገኘው ነጥብ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በጨዋታው ወደ ግብ ክልል ቶሎ ቶሎ በመድረስ የተሻሉ ሙከራዎችን በማድረግ  ተጋጣሚያቸውን ማስጨነቅ ቢችሉም  አጋጣሚውን በአግባቡ ባለመጠቀማቸው ለሽንፈት መዳረጋቸውን የተናገሩት ደግሞ የወልቂጤ ከተማ አሰልጣኝ ደረጀ በላይ ናቸው፡፡

ደጋፊዎችም  በሜዳዉ ተገኝቶ ስፖርታዊ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ ቡድናቸውን አበረታትተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም