በጋምቤላ የስፖርት ዘርፍን ለማጠናከር ተገቢው ድጋፍ ይደረጋል- ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ታንኳይ ጆክ

87

ጋምቤላ ሚያዝያ 3/2011 በጋምቤላ ክልል የስፖርቱን ዘርፍን በማጠናከር ብቁ ተወዳዳሪዎችን ለማፍራት ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደረግ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ታንኳይ ጆክ አስታወቀ።

በሦስተኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ቤቶች ስፖርት ውድድር ክልሉን ወክለው ለተሳተፉ ስፖርተኞች ትላንት የእራት ግብዥ ተደርጎላቸዋል ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንደገለፁት የስፖርቱን ዘርፍ በማጠናከር ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ብቁና ተወዳዳሪዎችን ለማፍራት ተገቢው ድጋፍ ይደረጋል ።

"በክልሉ በተለይም በእግር ኳስ ፣ በቦሊቦልና ቅርጫት ኳስ የተሻለ አቅም ያላቸው ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት የሚያስችል አቅም አለ " ብለዋል ።

የክልሉ መንግስት ዘርፉን በማጠናከር ከክልል አልፎ በአገርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ትከረት መስጠቱን ተናግረዋል ።

በሦስተኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ቤቶች ውድድር ክልሉን ወክሎ የተሳተፈው የስፖርት ልዑክ ላስመዘገው ውጤት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶማስ የማሎ በበኩላቸው ተማሪዎች ከትምህርታቸው በተጓዳኝ ስፖርታዊ ውድድሮችን ማድረጋቸው ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከርም የጎላ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ሀገር አቀፍ የስፖርት ውድድሩ የተማሪዎችን እርስ በእርስ ግንኙነት ከማሳደግ ባለፈ በመካከላቸው  የባህልና እውቀት ልውውጥ ለማድረግ አስተዋጽኦ እንዳለውም አመልክተዋል።

"ክልሉን የወከለው የስፖርት ልዑክ በውድድሩ በውሃ ዋናና ቴኳንዶ ካስመዘገበው ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ በተጨማሪ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወክለው የሚወዳደሩ አራት ስፖርተኞችን ለፌደራል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስመርጧል" ብለዋል ።

ትግራይ  በተካሄደው ሀገር አቀፍ የትምህርት ቤቶች ስፖርት ውድድር ክልሉን ወክሎ የተሳተፈው የስፖርት ልዑክ ሁለት የወርቅ፣ አንድ ብርና 16 የነሐስ ሜዳሊያዎችን ማግኘቱ ታውቋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም