ወጣቶች መንግስት የስራ ዕድል እንዲፈጥርላቸው ተጠየቀ

59

ነቀምቴ ሚያዚያ 3/2011 ትምህርት አጠናቀው ለሚገኙ ወጣቶች መንግስት የስራ ዕድል እንዲፈጥርላቸው የነቀምቴ ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ጠየቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ ከወለጋ ስታዲየም ምርቃት መልስ የነቀምቴ ከተማና የአከባቢው ነዋሪዎችን እያወያዩ ነው።

በውይይቱ ነዋሪዎች እንዳነሱት፤ የምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል ትልቁ ችግር የስራ አጥነት ነው።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በፌዴራል ደረጃ የመጣው ለውጥ ወደታች መውረድ እንዳለበት ገልጸዋል።

የወለጋ ህዝብ ከለውጥ አመራሩ ጎን እንደተሰለፈ የገለጹት ተሳታፊዎቹ ለውጡን የመቀልበስ ዓላማ ያላቸው ሃይሎች በመካከል በመግባት ህዝቡን ከአመራሩ ጋር ለማጣላት እንደሚሞክሩ ጠቁመዋል።

በፌደራል ደረጃ የታየው የሴቶች የአመራርነት መዋቅር በተለይ በነቀምቴ ከተማ እንዲሠራበት እና ሙስና እንዲቀንስ መንግስት ጠንክሮ እንዲሰራ ጠይቀዋል።

የነቀምቴ ከተማና አከባቢዋ የስራ አጥነት ችግር ያነሱት ነዋሪዎቹ በተለይም የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ዝግጅት እያላቸው በከተማ ጎዳና ላይ የፈሰሱት ወጣቶች መንግስት በአፋጣኝ የስራ ዕድል እንዲፈጥርላቸው ጠይቀዋል።

ውይይቱ የቀጠለ ሲሆን በነዋሪዎቹ ለተነሱ ጥያቄዎች የክልሉ ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም