የኢሉ አባቦር ዞን ዓመታዊ የስፖርት ውደድር ተጠናቀቀ

63

መቱ ሚያዝያ 2/2011 በኢሉአባቦር ዞን  በ13 ወረዳዎች መካከል ለአንድ ሳምንት ሲካሄድ የቆየው ዓመታዊ የልዩ ልዩ ስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ።

በእግር ኳስ ፣ ቦሊቦል ፣ ጠረጴዛ ቴኒስ፣ ብስክሌት፣አትሌቲክስ ጨምሮ በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች በተካሄደው ውድድር በሁለቱም ጾታ 563 ስፖርተኞች ተሳትፈዋል ።

በውድድሩ ዞኑን ወክለው ነቀምቴ ላይ በሚካሄደው የመላው ኦሮሚያ ስፖርት ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉ 50 ስፖርተኞች ተመርጠዋል ።

በማጠናቀቂያው ላይ በተካሄዱ ውድድሮች በወንዶች አንደኛ ዲቪዚዮን የመቱ ከተማ በእግር ኳስና  ጠረጴዛ ቴኒስ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም