የተባበሩት አረብ አሚሬቶች 118 ኢትዮጵያውያን እስረኞችን ልትፈታ ነው

48
ግንቦት25/2010 በተባበሩት አረብ ኤምረቶች በተለያዩ ጥፋቶቸ  ተከሰው የተፈረደባቸውና ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የነበሩ 118 ኢትዮጵያውያን ሊፈቱ ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ከእስር የሚፈቱት ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፡፡ ኢትዮጵያውያኑ የሚፈቱት  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቅርቡ በተባበሩት አረብ ኤምረቶች ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለአገሪቱ  መንግስት  ባቀረቡት  ጥያቄ  መሠረት  መሆኑም ተጠቅሷል፡፡ በተባበሩት አረብ ኤምረቶች የሚገኘው የኢፌዴሪ ኤምባሲ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው መሆኑም ተመልክቷል፡፡ ቀደም ሲል በተመሳሳይ በተደረገ ጥረት ከ2000 በላይ ኢትዮጵያውያን ከሱዳንና ሳውዲ አረቢያ ተፈተዋል፡፡ በቀጣይም በተለያዩ አገሮች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መብታቸው  እንዲከበር  አስፈላጊው  ዜጋ ተኮር የዲፕሎማሲ ስራ እንደሚሰራ ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም