ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ 25ተኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ላይ ይካፈላሉ

104

አዲስ አበባ መጋቢት 29/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ 25ተኛ ዓመት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ እንደሚካፈሉ ተገለጸ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው  ትላንት ወደ ሩዋንዳ ማቅናታቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትላንትናው እለት ሩዋንዳ ኪጋሊ ሲገቡ የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖልካጋሜ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሩዋንዳ በእርስ በርስ ግጭት 800 ሺህ ዜጎቿ የተጨፈጨፉበትን 25ኛ ዓመት መታሰቢያ  በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረች ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይን ጨምሮ የሌሎች ሀገራት መሪዎችም የዝግጅቱ ታዳሚዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም