የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ እንዲጸድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ

118

አዲስ አበባ መጋቢት28/2011 የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ እንዲጸድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል።

ምክር ቤቱ ባካሄደው 67ኛ መደበኛ ስብሰባ የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

የጦር መሳሪያ ቁጥጥር የአገርንና የህዝብን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም የዜጎችን እና የህዝቦችን መብትና ደህንነት ለማስከበር አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ ግለሰቦች የታጠቋቸውን መሳሪያዎች የህብረተሰቡን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ ተግባር ሊውሉ የሚችሉበትን እድል መፍጠር አስፈላጊ ነው ብሏል።

በስራ ላይ ባሉ ህጎችና አሰራሮች ላይ ያልተፈተሹ ጉዳዮች በዝርዝር ህግ መደንገግና ወጥነት ያለው ስርአት መፍጠር በማስፈለጉ እንዲሁም ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸውን ህገ ወጥ የመሳሪያ ቁጥጥርን የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ለማስፈጸምና ዓለም አቀፍ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋትም እንዲሁ።

በነዚህ መነሻዎች የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም