አየር መንገዱ ለሰባተኛ ጊዜ የአፍሪካ አስተማማኝ አየር መንገድ ሽልማትን ተቀዳጀ

102
አዲስ አበባ ግንቦት 24/2010 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦምባርዴር ኤሮስፔስ ከተሰኘ ድርጅት የ2017 የአስተማማኝነት ብቃት ሽልማት ተቀበለ። አየር መንገዱ ሽልማቱን ላለፉት ሰባት ተከታታይ ዓመታትም ሲወስድ መቆየቱን አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም "ለሰባት ተከታታይ ዓመታት ሽልማቱን መቀበላችን የድርጅታችን ሰራተኞች ያደረጉት ተከታተይና ብርቱ ጥረት ፍሬ በመሆኑ ደስታችን ከፍ ያለ ነው" ብለዋል። አየር መንገዱ ለደንበኞቹ አስተማማኝ የበረራ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ ነው ያሉት አቶ ተወልደ፤ ሽልማቱ "ለአፍሪካና ለአገር ውስጥ በረራችን ልቀት ቃል የምንገባበት ነው"ም ብለዋል። በአሁኑ ወቅት '21 ኪው-400' አውሮፕላኖች አገልገሎት የሚሰጠው አየር መንገዱ፤ በሞተራቸው ጥራት ተመራጭ ከሆኑ አውሮፕላኖች የሚመደበውን የ'ኪው-400' አውሮፕላን አገልግሎት በመስጠት በአፍሪካ ብቸኛ ነው። የበረራ አስተማማኝነት ብቃት ሽልማት በቦምባርዴር የአገር ውስጥ በረራ ጀቶችና አውሮፕላኖች በመጠቀም በማጓጓዝ በአገልግሎታቸው ፍጥነትና ብቃት ለአየር መንገዶች የሚሰጥ ዕውቅና ነው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም