አቶ ኡመር ሁሴን የኦዴፓ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሆነው ተመረጡ

112

መጋቢት 19/2011 የኦሮሚያ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባካሄደው ስብሰባ በዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ምትክ አቶ ኡመር ሁሴንን የኮሚቴው አባል አድርጎ መርጧል።

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኦዴፓ) ጽ/ቤት ሃላፊ ዶክተር አለሙ ስሜ በዚህ ጉዳይ ላይ ለሚዲያዎች ማብራሪያ መስጠታቸውን የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

በዚሁ መሰረት የኦዴፓ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች፡-

  1. ዶክተር አቢይ አህመድ
  2. አቶ ለማ መገርሳ
  3. አቶ ኡመር ሁሴን
  4. ዶክተር አለሙ ስሜ
  5. አቶ ሽመልስ አብዲሳ
  6. አቶ አዲሱ አረጋ
  7. ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
  8. አቶ ፍቃዱ ተሰማ
  9. አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ  መሆናቸው ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም