ፔንታገን በአሜሪካና ሜክሲኮ ድንበር ለሚሠራው ግንብ 1 ቢሊየን ዶላር መደበ

79

መጋቢት 17/2011  የአሜሪካ ወታደራዊ መስሪያ ቤት ፔንታገን በአሜሪካ-ሜክሲኮ ድንበር ለሚገነባው አዲስ ግንብ 1 ቢሊየን ዶላር መመደቡ ተነግሯል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካና በሜክሲኮ ድንበር መካከል ግንብ ለመገንባት የአስቸኳይ ጊዜ ገንዘብ እንዲመደብ ካወጁ ወዲህ ፔንታገን ገንዘብ ሲመድብ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

ትራምፕ በሁለቱ ሀገራት መካከል የግንብ አጥር እንደሚገነቡ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ሲናገሩ እንደነበር ይታወሳል።

የዴሞክራት ፓርቲ ተወካዮች የትራምፕን እንቅስቃሴ ተቃውመውታል።

ፔንታገን የመደበው ገንዘብ 91 ኪሎ ሜትር ርዝመት ላለው የግንብ አጥር ግንባታ እንደሚውል ነው የተመላከተው።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በአሜሪካ ደቡባዊ ድንበር ተሻግረው ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ወንጀለኞች ቀውስ እየፈጠሩ በመሆኑ የግንብ አጥር እንዲገነባ ሲወተውቱ ሰንብተዋል።

ለዚህ ግንባታ ወጪ ያቀረቡት የ5.7 ቢሊየን ዶላር በጀት ጥያቄ በኮንግረሱ ውድቅ በመሆኑ  የአቸኳይ ጊዜ ገንዘብ እንዲመደብ ማወጃቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ቢቢሲ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም