የወላይታ ልማት ማህበር ባከናወናቸው የልማት ሥራዎች ተጠቃሚ ሆነናል...ነዋሪዎች

239

ሶዶ መጋቢት 16/2011 የወላይታ ልማት ማህበር ባከናወናቸው የተለያዩ የልማት ተግባራት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስተያየታቸውን የሰጡ የዞኑ ነዋሪዎች ገለጹ። 

ልማት ማህበሩ በበኩሉ ባለፉት አመታት ከ440 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርናና በመሰረተ ልማት ተቋማት ግንባታ ባከናወናቸው ተግባራት ከ700 ሺህ በላይ የዞኑን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል።

ልማት ማህበሩ 18ኛ የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ያከናወናቸውን የልማት ሥራዎች ለአባላቱና ለደጋፊዎቹ አስጎብኝቷል፤ ዘንድሮ ለሚያስገነባው ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግና የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠና ማዕከልም የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

በዞኑ ሁምቦ ወረዳ አምፖ ኮይሻ ቀበሌ የሚኖሩት አርሶ አደር ሳፐነ ሳሙኤል1 ነጥብ 5 ሄክታር የእርሻ መሬት ቢኖራቸውም በዕውቀት ክፍተት ምክንያት በዓመት አንዴ ብቻ ቦቆሎ ሲያመርቱ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከልማት ማህበሩ የክህሎት ስልጠና፣ ምርጥ ዜርና ግብአት ማግኘት ከጀመሩ ከሁለት ዓመት ወዲህ ምርታማነትን ሊያሳድግ የሚችል በቂ ዝግጅት በማድረግ እንደ ቲማትምና በርበሬ ያሉ የጓሮ አትክልቶችን በሦስት ዙር በመትከል በዓመት እስከ 50 ሺህ ብር ትርፍ ማግኘት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡

እንደ አርሶ አደሩ ገለጻ ቤተሰባቸውን በአግባቡ ለማስተዳደርና ልጆቻቸውን በሚገባ ለማስተማር በአሁኑ ወቅት የተሻለ አቅመ ፈጥረዋል።

የልማት ማህበሩ በተለይም በትምህርት መስክ ባከናወናቸው ተግባራት የአካባቢው ነዋሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ በዞኑ የዳሞት ጋሌ ወረዳ ነዋሪ አቶ ተፈራ በየነ ናቸው፡፡

ማህበሩ የመማር አቅም የሌላቸውንና ዕድሉን ያላገኙ ህጻናትን ተቀብሎ በማስተማር ለከፍተኛ ደረጃ ማብቃቱን ገልጸው የማህበሩ ሥራዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ሕብረተሰቡም ድጋፉን እንዲያጠናክር አመልክተዋል፡፡

ከአምስት ዓመት በፊት ባልተለመደ መልኩ በእግራቸው ላይ የጤና ችግር ገጥሟቸው እንደልብ ለመንቀሳቀስ ተቸግረው እንደነበር ያስታወሱት ደግሞ ወይዘሮ አየለች ዳንሳ ናቸው።

የልማት ማህበሩ ባደረገላቸው ድጋፍ ጤናቸው በአሁኑ ወቅት መመለሱን የገለጹት ወይዘሮ አየለች፣ የልማት ማህበሩ ለእርሳቸው ብቻ ሳይሆን ለብዙዎችም አለኝታ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

የልማት ማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ጢሞቲዮስበበኩላቸው ማህበሩ  በመንግስት ሊሸፈኑ የማይችሉ የልማት ክፍተቶችንና ፍላጎቶችን ለማሟላት ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ጠቁመዋል።

"በሰው ሃብት ልማት፣ በዘላቂ የኑሮ ማሻሻያና በተቀናጀ ጤና ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የዞኑን ነዋሪዎች ተጠቃሚ አድርጓል" ብለዋል፡፡  

በትምህርቱ ዘርፍ በቅድመ መደበኛ ከ400 በላይ ተማሪዎችን እንዲሁም በወላይታ ሶዶ ከተማ በተገነባው ሊቃ ትምህርት ቤት ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ከፍተኛ ውጤት ያመጡና የመማር ዕድል ያጡ ከ500 በላይ ተማሪዎችን በመቀበል በሳይንስ መስክ እያስተማረ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።

"በሁምቦ ወረዳ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ባስገነባው የግብርና ክህሎት ማሳደጊያ ማዕከል አርሶ አደሩ የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም በሚችሉበት መንገድ ላይ ግንዛቤውን የማሳደግ ስራ ተሰርታል" ብለዋል።

በእዚህም አርሶ አደሮች በሰብል ልማት፣ በእንስሳት እርባታ፣ በንብ ማነብና በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እንዲሰማሩ መደረጉን ነው ያመለከቱት።

አቶ ሀብታሙ እንዳሉት ማህበሩ በጤናው መስክ የመንግስትን የጤና ፖሊሲ በመደገፍ እንደ በኤች አይቪ/ኤድስ ባሉ ተላላፊ በሽታዎች ላይ የበኩሉን እገዛ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሰረተ ልማት መስክ ማህበሩ በወላይታ ሶዶ ከተማ 10 ነጥብ 75 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ በማስገንባት ለአግለግሎት ማብቃቱንና በአሁኑ ወቅትም የ14 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ሥራ በማከናወን ላይ መሆኑን አስረድተዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪና የልማት ማህበሩ የበላይ ጠባቂ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ በበኩላቸው ማህበሩ ከመንግስት ጎን በመሆን ባከናወናቸው የልማት ስራዎች የዞኑን ነዋሪዎች ተጠቃሚ እያደረገ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡       

የማህበሩ የልማት ተግባራት መንግስት ለሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች አጋዥ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ዳጋቶም ከማህበሩ አባላት በተጨማሪ የሚመለከታቸው አካላት ለማህበሩ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ አመልክተዋል።

ከጉብኝቱ በተጨማሪ ማህበሩ በ2018 በጀት ዓመት ባከናወናቸው የልማት ሥራዎች ላይ የውጭ ኦዲት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራትና የድጋፍ አሰባሰብ አቅጣጫም ተቀምጧል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

ባህር ዳር መጋቢት 16/2011 የወላይታ ልማት ማህበር ባከናወናቸው የተለያዩ የልማት ተግባራት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስተያየታቸውን የሰጡ የዞኑ ነዋሪዎች ገለጹ። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም