የመከላከያ ደንብ ልብስ በመልበስ ለዘረፋ ተዘጋጅተዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

103

አምቦ  መጋቢት 16/2011 የመከላከያ ደንብ ልብስ በመልበስ  ለዘረፋ ተዘጋጅተዋል ያላቸውን ሁለት ተጠርጣሪዎችን  መያዙን የአምቦ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማው ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ተሬሳ ካሳዬ ለኢዜአ እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ትናንት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ተኩል አካባቢ ነው ።

ፖሊስ ከህብረሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በከተማው ቀበሌ ሁለት አራዳ  በሚባለው አካባቢ መኖሪያ ቤታቸው ነው የተያዙት፡፡

"አንድ ሽጉጥ፣ አራት ላፕቶፖ ኮምፒውተሮች፣ ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮችና የመከላከያ ደንብ ልብሶች በተጠርጣሪዎች እጅ በኤግዚቢትነት ተይዘዋል" ብለዋል ።

እነዚህ ሴትና ወንድ ተጠርጣሪዎች እንደ ባለትዳር አብረው እንደሚኖሩ የተናገሩት ረዳት ኮሚሽነሩ የመከላከያ የደንብ ልብስ በመልበስ ህብረተሰቡን በማስፈራራት ለመዝረፍ ተዘጋጅተው እንደነበር ገልጸዋል ።

ፖሊስ  ተጠርጣሪዎችን በመያዝ  ጉዳያቸውን እያጣራ  መሆኑን አመልክተው ህብረተሰቡ አጠራጣሪ የሆኑት ድርጊቶች ሲያጋጥሙት ለፖሊስ በማሳወቅ እያሳየ ያለውን የወንጀል መከላከል ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም