መቀሌ 70 እንደርታና ወልዋሎ ዩኒቨርሲቲ ዓዲግራት አንድ ለአንድ ተለያዩ

328

መቀሌ መጋቢት 15/2011 በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ በትግራይ ስታዲዬም ዛሬ የተገናኙት መቀሌ 70 እንደርታና ወልዋሎ ዩኒቨርስቲ ዓዲግራት አንድ ለአንድ  ተለያይተዋል።

በጨዋታው ማጠቃለያ ላይ በደጋፊዎች መካከል ተከሰቶ የነበረው ግጭት ከስፖርት ደጋፊው ማህበረሰብ የማይጠበቅ ነው ሲሉ ደጋፊዎች ተናግረዋል።

የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ18ኛው ደቂቃው እንየው ካሳሁን፣መቀሌ 70 እንደርታ ክለብ በ30ኛው ደቂቃ በያሬድ ከበደ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በጨዋታው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ የተሻለ እንቅስቃሴና የግብ ሙከራ በማድረግ የተሻለ ነበር።

በጨዋታው ማብቂያ በክለቦቹ ደጋፊዎቸ መካከል ግጭት ተፈጥሮ ነበር።

የመቀለ 70 እንደርታ ደጋፊ ብርሃኑ ኪዳኑ በደጋፊዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ማዘኑን ተናግሯል።

የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ እግር ኳስ ደጋፊ ሀብታሙ ተጠምቀ በበኩሉ ሁከትና ግርግር ለመፍጠር የሞከሩ ደጋፊዎች በፀጥታ ማስከበር ሥራ ላይ ከነበሩ ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውን አስረድቷል።

በክለቦቹ መካከል ያለውን ችግር በማጥናት ዘላቂ መፍትሄ መስጠት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

በክለቦቹ ደጋፊዎች መካከል ተከስቶ በነበረው ግጭት በሕይወትና አካል ላይ ጉዳት አላደረሰም።