ሚኒስቴሩ በገደብ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ሦስት ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

49

ዲላ  መጋቢት 15/2011 የሴቶች፣ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ሦስት ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ።

የሚኒስቴሩ አመራርና ሠራተኞች  ከሜር ጆይ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያሰባሰቡትን የምግብ፣ የአልባሳትና የቁሳቁስ ድጋፍ  ያስረከቡት ትናንት ነበር።

የሴቶች፣ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ዴኢታ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት የተፈናቃዮችን ችግር ለማቃለል  በተለይም በእናቶችና በሕጻናት ከሚያደርሰው አደጋ ለመታደግ ሚኒስቴሩ ባለሙያዎችን በመመደብ  እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

ለተጎጆዎች የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚጠናከርም ወይዘሮ ስመኝ ተናግረዋል።

የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ በበኩላቸው ''የእኛ ልጆች በትምህርት ቤት ጊዜያቸውን እያሳለፉ፤ የእናንተ ልጆች ሜዳ ላይ ወድቀው ማየት ልብ ይሰብራል'' በማለት በተፈናቃዮቹ  ሁኔታ የተሰማቸውን ስሜት ገልጸዋል።

ሌሎች አካላትን በማሰተባበር  ተፈናቃዮቹ ያሉበትን ሁኔታ ለመቀየር ድርሻቸውን ለመወጣትም ቃል ገብተዋል።

በጉብኝቱም ዳያስፓራዎች፣ አርቲስቶችና ታዋቂ ሰዎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም