በቤንች ማጂ ዞን የሚታዩትን የሰላምና የጸጥታ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት አመራሩ ሚናውን እንዲወጣ ተጠየቀ

79

ሚዛን  መጋቢት 15/2011 በቤንች ማጂ ዞን የተከሰቱትን የሰላምና ጸጥታ ችግሮች በዘላቂነት በመፍታት አመራሩ ሚናውን እንዲወጣ የደቡብ ከልል መንግሥት አንድ የሥራ ኃላፊ አስገነዘቡ።

የወረዳ አመራሮች የተሳተፉበት ውይይት ትናንት በሚዛን ከተማ ተጀምሯል።

የደቡብ ክልል ቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ክፍሌ ገብረማርያም በዚህ ወቅት እንዳሳሰቡት በዞኑ እየገጠሙ ያሉት ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ በየደረጃው የሚገኝ አመራር ሚናውን መወጣት ይገባዋል። 

የአመራር አካላት የግጭትና ያለመግባባት ምክንያት ሳይሆኑ መፍትሔ አመንጪ የለውጥ አካላት መሆን አለባቸው ብለዋል።

ማንኛውም ጉዳይ ከሕዝብ ጥቅም አንጻር ሊታይ እንደሚገባ ያመለከቱት አቶ ክፍሌ፣ የሕዝቡ ስጋት የሆኑ የሰላምና ጸጥታ ችግሮች ለማስወገድ ተግቶ መሥራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

አመራሩ የሕዝብ አደራውን የሚወጣው የባከነውን ጊዜ በሥራ ማካካስ እንደሚጠበቅበትም ኃላፊው አስገንዝበዋል።

የቤንች ማጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስራት አሰፋ በበኩላችው ወይይቱ የዞኑን ያሉ የሰላምና የጸጥታና ችግሮች ለመፍታት እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው መድረክ የዞንና የወረዳ አመራሮች እየተሳተፉበት ነው፡፡

የቤንች ማጂ ዞን ከአገራዊው ለውጥና የማንነት ጥያቄ በሚያነሱ ወገኖች ግጭቶች ሲፈጠሩበት መቆየቱ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም