የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተፈናቀሉ ዜጎች 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

51

አዲስ አበባ መጋቢት 14/2011 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላ አገሪቷ ለተፈናቀሉ ዜጎች 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ባጫ ጊና በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በአገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች ባንኩ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል።

የድጋፍ ክፍፍሉ የተደረገውም ከብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የተገኘውን የተፈናቃዮች ቁጥር መሰረት በማድረግ  መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም