ብሪታንያ በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን ለውጥና ብሔራዊ መግባባት ትደግፋለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ - ኢዜአ አማርኛ
ብሪታንያ በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን ለውጥና ብሔራዊ መግባባት ትደግፋለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ
59
ግንቦት 24/2010 የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ ሀገራቸው በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን ለውጥና ብሔራዊ መግባባት እንደምትደግፍ ገለጹ፡፡ የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያው አቻቸው ዶክተር አቢይ አህመድ ጋር የስልክ ውይት አድርገዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሯ ቃል አቀባይ እንዳሉት በውይይታቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ ሌሎች እስረኞች በምህረትና ይቅርታ መለቀቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሯ አድንቀዋል፡፡ እንግሊዝ ትምህርትን ለማጎልበት፣ ኢኮኖሚያዊ ለውጡን ለማፋጠን፣ ኢንዱስትሪውን ለማስፋፋት፣ የሙስና ትግሉን ለማጠናከርና የስራ ፈጠራን ለማበረታታት ድጋፍ በምታደርግባቸው ሁኔታዎችና በሌሎች የልማት ድጋፎች ዙሪያ መወያየታቸውም ተገልጿል፡፡ ሁለቱ ሀገራት የንግድ ግንኙነታቸውን የበለጠ ማጠናከርና የኢትዮጵያን የልማት አጀንዳ ለማሳካት በተለይ በመሰረተልማትና በፋይናንስ ዘርፍ ብሪታኒያ ያላትን ሙያዊ ድጋፍ በምታበረክትበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውንም ስታንዳርድ አስነብቧል።