መርካቶን ከገበያ ማእከልነቱ ባሻገር ምቹ የመዝናኛ አካባቢ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት ሊካሄድ ነው

53

አዲስ አበባ 13/2011 በመርካቶ ገበያ የሚታየውን የትራፊክ ፍሰት የተሳለጠ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት ሊያካሄድ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ገለጸ።

ጥናቱ መርካቶን ከግብይት ማዕከልነት ባሻገር ለመዝናኛ ምቹ ለማድረግ እንደሚያስችልም ተገልጿል።

ጥናቱ ተጠናቆ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲደረግ በመርካቶና አካባቢው የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ በማስቀረት የተሳለጠ የተሽከርካሪ ፍሰትና የሰዎች እንቅስቃሴ እንዲኖር ያደርጋል ተብሏል።

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የዲዛይን ዳይሬክተር ኢንጅነር ረሺድ ሙሰማ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት በጥናቱ አበሻ አለርት የተባለ ተቋም በአማካሪነት ይሰራል።

ጥናቱ በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ከተከናወነ በኋላ ግንባታው በሁለት ዓመታት ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑንም ገልጸዋል።

እንደ ኢንጂነር ረሺድ ገለፃ የፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ መርካቶን ከገበያ ማዕከልነቷ ባሻገር ሰዎች ሊዝናኑባት የሚችሉባት ተመራጭ አካባቢ ያደርጋታል።

የጋዎፍ ዳይሬክተር ሚስተር ፖል ምቢያ በበኩላቸው ታላቁን የአፍሪካ የገበያ ማዕከል ለማዘመን ኩባንያቸው ጥናቱን እንዲያከናውን በመመረጡ መደሰታቸውን ተናግረዋል።

ጋወፍ የተሰኘው ተቋም በዘርፉ ከ50 ዓመት በላይ ልምድ ያለውና በኢትዮጵያም ከአስራ አምስት ዓመት በላይ የሰራ ድርጅት መሆኑን ኢንጅነር ረሽድ ሙሰማ ተናግረዋል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ በዓለም ባንክ ድጋፍ የሚሸፈን ሲሆን ወጪው ከጥናቱ በኋላ የሚታወቅ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም