የጋህአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው

60

ጋምቤላ መጋቢት 11/2011 የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጋህአዴን/ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ማካሄድ ጀመረ፡፡

የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እንዳሉት ማዕከላዊ ኮሚቴው የ2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸምን ይገመግማል፡፡

ድርጅቱ በተለይም እንደ አገር የተጀመረውን ለውጥ፣ ሪፎርምና አደረጃጀት እውን ከማድረግ አኳያ የተጓዘበትን ሂደት ይመለከታል፡፡

እንዲሁም የቀጣይ ወራት የተከለሰ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ በተለይም በክልሉ ፀጥታ ዙሪያ ተወያይቶ  አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ሊቀመንበሩ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም