ተፈናቃዮችን ለሦስተኛ ዙር መልሶ የማቋቋም ስራ ሊጀመር ነው

70

አዲስ አበባ መጋቢት 11/2011 በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የሦስተኛ ዙር የመልሶ ማቋቋም ስራ እንደሚጀመር የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት 2 ነጥብ 7  ሚሊዮን ያህል ዜጎች ከኑሯቸው ተፈናቅለዋል።  አብዛኛዎቹ የተፈናቀሉት ከአገሪቱ ደቡብ ምእራብና ምስራቅ ክፍሎች ነው።

በመሆኑም ሚኒስቴሩ የዜጎች መፈናቀል በተከሰተባቸው ሰባት ክልሎችና አንድ የከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ 38 ዞኖች ላይ ለአንድ ወር የሚቆይና ተፈናቃዮችን ለማቋቋም የሚያስችል መርሃ ግብር ሊጀምር መሆኑን ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ አመልክቷል።

የመልሶ ማቋቋም ተግባሩ ሚኒስትሮችን፣ ከፍተኛ የአመራር አካላትን፣ የክልል መንግስታት እና ሌሎች ባለድርሻዎችን ያካተተ ነው። 

ህዝብ ለህዝብ የሚደረገውን ድጋፍ አጠናከሮ ማስቀጠል፣ አካባቢያዊ አቅርቦቶችን መጠቀም፣ ንብረት ለወደመባቸው ዜጎች መፍትሄ ማፈላለግና የማቋቋም ስራውን ክልሎች በባለቤትነት እንዲመሩት ማድረግ ከሚከናወኑ ተግባራት ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው። 

ሚኒስቴሩ ከህዳር ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ የተፈናቃዮችን ሰብዓዊ መብት እና ዋስትና ለመጠበቅ በሰባት ክልሎችና በአንድ ከተማ አስተዳደር 40 ከፍተኛ ባለሙያዎችን በመመደብ የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ግብዓቶች የማቅረብ ስራ ሲሰራ ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት በአገር ውስጥ መፈናቀል ላይ የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የክልል አመራሮች፣ የክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽንና ለሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማወያየት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ የማቋቋሚያ ዕቅድ አዘጋጅቷል።

ዕቅዱ የህግ የበላይነትን የማስከበርና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ግቦች እንዳሉትም ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

የተፈናቀሉ ዜጎች ይኖሩባቸው የነበሩበትን አካባቢዎች ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በፍጥነት ወደቀያቸው የሚመለሱ፣ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የሚመለሱ እንዲሁም ተጨማሪ ስራ የሚያስፈልጋቸውን በመለየት በፍጥነት ወደ ተግባር ለመግባት የሚያስችል ውይይት ማካሄዱን አስታውቋል። 

አዲስ አበባ መጋቢት 11/2011 በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለሶስተኛ ዙር መልሶ የማቋቋም ሥራ እንደሚጀመር የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት 2 ነጥብ 7  ሚሊዮን ያህል ዜጎች ከኑሯቸው ተፈናቅለዋል።  አብዛኛዎቹ እነዚህ ሰዎች የተፈናቀሉት ከአገሪቱ ደቡብ ምእራብና ምስራቅ ክፍሎች ነው።

በመሆኑም ሚኒስቴሩ የዜጎች መፈናቀል በተከሰተባቸው ሰባት ክልሎችና አንድ የከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ 38 ዞኖች ላይ ለአንድ ወር የሚቆይና ተፈናቃዮችን ለማቋቋም የሚያስችል መርሃ ግብር ሊጀምር መሆኑን ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ አመልክቷል።

የመልሶ ማቋቋም ተግባሩ ሚኒስትሮችን፣ ከፍተኛ የአመራር አካላትን፣ የክልል መንግስታት እና ሌሎች ባለድርሻዎችን ያካተተ ነው። 

ህዝብ ለህዝብ የሚደረገውን ድጋፍ አጠናከሮ ማስቀጠል፣ አካባቢያዊ አቅርቦቶችን መጠቀም፣ ንብረት ለወደመባቸው ዜጎች መፍትሄ ማፈላለግና የማቋቋም ስራውን ክልሎች በባለቤትነት እንዲመሩት ማድረግ ከሚከናወኑ ተግባራት ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው። 

ሚኒስቴሩ ከህዳር ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ የተፈናቃዮችን ሰብዓዊ መብት እና ዋሰትና ለመጠበቅ በሰባት ክልሎችና በአንድ ከተማ አስተዳደር 40 ከፍተኛ ባለሙያዎችን በመመደብ የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ግብዓቶች የማቅረብ ስራ ሲሰራ ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት በአገር ውስጥ መፈናቀል ላይ የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የክልል አመራሮች፣ የክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽንና ለሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማወያየት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ የማቋቋሚያ ዕቅድ አዘጋጅቷል።

ዕቅዱ የህግ የበላይነትን የማስከበርና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ግቦች እንዳሉትም ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

የተፈናቀሉ ዜጎች ይኖሩባቸው የነበሩበትን አካባቢዎች ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በፍጥነት ወደቀያቸው የሚመለሱ፣ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የሚመለሱ እንዲሁም ተጨማሪ ስራ የሚያስፈልጋቸውን በመለየት በፍጥነት ወደ ተግባር ለመግባት የሚያስችል ውይይት ማካሄዱን አስታውቋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም