በጥቂት አደጋዎች የተፈተነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወርቃማ ታሪክ

304

ቁምልኝ አያሌው (ኢዜአ)

የሰውን ልጅ እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ቀላልና ቀልጣፍ ለማድርግ በሚያስችል መልኩ  አሁን በምንኖርባት አለም በተለያዩ የቴክኖሎጂ ዘርፍች ላይ እውቀታቸውን ፈሰስ በማድረግ በርካታ ስራዎቻቸውን አበርክተዋል፡፡

ከነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከልም በትራንስፖርትና ማጓጓዣ ዘርፍ ላይ እጅግ ተመራጭና አስተማማኝ በመሆን የሚታወቀው  አንዱ አውሮፕላን ሲሆን ዘርፈ ብዙ የሆኑ አገልግሎቶችን በመስጠትም ግንባር ቀደም ከሚባሉት የቴክኖሎጂ ውጤቶችም አንዱ ነው፡፡

በዚህ ሂደትም የተለያዩ አለም አቀፍ ሃገራት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖሊቲካዊ፣ ማህበራዊ ብሎም ባህላዊ የሆኑ የመልካም መስተጋብራዊ ግንኙነታቸውን ቀልጣፍና ፈጣን በሆነ መንገድ ለማከናወን በሚያስችል መልኩ ስለሚያካሂዱበት ይህኛው የትራንስፖርት ዘርፍ እጅግ ተመራጭ በመሆኑ አብዛኛውን ጊዜም አገልግሎቱን ይጠቀሙበታል፡፡

ኢትዮጵም ይህንን የትራንስፖርት ዘርፍ  በመቀላቀል ለዘመናት ስትጠቀምበትና አገልግሎትም ስትሰጥበት ቆይታለች፡፡

በመሆኑም ሃገራችን ዘርፉን ለማጠናከርና ተወዳዳሪነትንም ጭምር ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ በርካታ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመግዛት  ስመ ጥር ከሆኑ አየር መንገዶች አንዱ በመሆን መልካም የሚባል አገልግሎቶችን በመስጠት  አየር መንገዳችን በአለም ላይ ካሉ አየር መንገዶች  ተመራጭና አስተማማኝ በመሆን አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያችን ብሎም አፍሪካ ብሄራዊ አርማ ተደርጎ የሚጠቀሰው  አየር መንገዱ ታህሳስ 1 ቀን 1938 ዓ/ም የተመሰረተ ስለመሆኑ የታሪክ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ይህ አየር መንገድ የአስተዳደር ሂደቱ የአሜሪካ ዜግነት ባላቸው አካላት ሲካሄድ የነበረ ሲሆን  ትራንስወርልድ ኤር ዌይስ ከሚባል አየር መንገድ ጋር በጋራ ሊመሰረት መቻሉንም በመረጃው ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

በምስረታ ሂደቱም የተለያየ መጠንና አይነት ያላቸው አውሮፕላኖችን ከአሜሪካ ወታደራዊ ሃይል ጋር ስምምነት በማድረግ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ያገለገሉ 5 ዲሲ 3ሲ47 አውሮፕላኖች በመግዛት አገልግሎት መስጠት ጀምሮ ነበር፡፡

አየር መንገዳችን የመጀመሪያ በረራውን ሀ ብሎ የጀመረውም በዚያው  በተመሰረተበት አመት መጋቢት 30 ቀን 1938 ዓ/ም ሲሆን በረራውም ከአዲስ አበባ ወደ ካይሮ የተደረገ በረራ ነበር፡፡

ከዚህ ጅማሮ በኋላ አየር መንገዳችን የበረራ አድማሱን በማስፍት በተለያዩ ክፍለ አለማት በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በኤዥያ እንዲሁም በአሜሪካ ጭምር መዳረሻ ሲኖሩት በአሁኑ ሰዓትም በጠቅላላው 117 እና ከዚያ በላይ መዳረሻዎች አሉት፡፡

በአህጉራችን አፍሪካ በተለያዩ ከ60 በላይ የሆኑ የክፍለ አህጉሩ ከተሞችን መዳረሻ በማድረግ ክፍተኛ ሚና ያላቸው አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ያለ አየር መንገድ ነው፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኘው የቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሃገራችን አየር መንገድ ዋና ማዕከል ያደረገ ሲሆን የዘርፍን ሙያተኞች ብቁ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ በራሱ ተቋም የአውሮፕላን አብራሪዎች አቬሽን ማስልጠኛ ተቋም በማደራጀት የግል አብራሪና የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ፈቃድ በመስጠት ምልካም የሚባል ተግባራቶችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በዘርፍ ለተሰማሩ የውጪ ሃገራት ዜጎች ስልጠና በመስጠት የአቬሽን ዘርፍን ከ40 አመታት በላይ ድጋፍ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፆ ያበረከተ ተቋም ነው፡፡

የሃገራችን አየር መንገድ ለመንገደኞች ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል መልኩ ከነባር አውሮፕላኖች እስከ ዘመናዊው ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች ጭምር ባለቤት በመሆን በአፍሪካ የቀዳሚነትን ቦታ ሲይዝ የ100 አውሮፕላኖች   ባለቤት በመሆን ሰፊ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡

በአቬሽን ዘርፍም የተወዳዳሪነት አድማሱን በማስፍት ከአፍሪካ ባሻገር  በአለም አቀፍ ደራጃ ከሚገኙ የዘርፍ ተቋማት ከቀዳሚዎቹ ተርታ በመሰለፍ ተጠቃሽና ተወዳዳሪ  እየሆነ የመጣ  አየር መንገድ ነው፡፡

በዚህ ሂደትም አየር መንገዳችን በአጠቃላይ ካካበተው ልምድና ተወዳዳሪነት በመነሳት ብዙዎቹ የአፍሪካውያን ኩራት ጭምር በማለት ይጠሩታል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም የሃገራችን ኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቬሽን ኢንዱስትሪው ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን በመስጠት ስመ ጥር ከሆኑ አየር መንገዶች ውስጥ አንዱ ሲሆን አየር መንገዳችን አገልግሎት በመስጠት በቆየባቸው 70 አመታት ውስጥ በታሪኩ ሊረሳቸው የማይችሉ በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠሙት 3 ከባድ አደጋዎች ብቻ ናቸው፡፡

የመጀመሪያው በ1989 ዓ/ም ከአዲሰ አበባ በመነሳት በናይሮቢ በማድረግ ወደ ሃገረ ህንድ የተደረገ በረራ ሲሆን የበረራ ቁጥር 961 በጠላፊዎች በተፈፀመ ድርጊት በህንድ ውቅያኖስ በምትገኘው የኮሞሮስ ደሴት አደጋ የደረሰበት ሲሆን በአጠቃላይ የ123 ሰዎች ህይዎት ያለፈበት እጅግ አስከፊ አደጋ ነበር፡፡

አየር መንገዳችን የደረሰበትን ሁለተኛ አደጋ ጥር 17 2002 ዓ/ም  የበረራ ቁጥር 409 መነሻውን ቤሩት አድርጎ ወደ ሰማይ በረራውን በጀመረ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ባልታወቀ ምክንያት በሜዲትራኒያን ባህር ላይ የሰመጠው አስከፊ የበረራ ክንውን ነበር፡፡

በሶስተኛ ደረጃ ተጠቃሽና እጅግ የብዙሃንን ልብ የሰበረው አስከፊ አደጋ ደግሞ ይህኛው ሰሞኑን መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ/ም የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የሆነ ቦይንግ 730 ማክስ 8 አውሮፕላን  በአጠቃላይ 157 መንገደኞችንና የበረራ አባላትን  በመያዝ መነሻውን  ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በማድረግ 2፡38 ደቂቃ በመነሳት ወደ ኬኒያ ናይሮቢ ጉዞው ላይ እያለ ከ6 ደቂቃዎች በኋላ ከራዳር ቁጥጥር ውጪ በመሆን ግንኙነትቱ ተቋርጦ ምክኒያቱ ሳይታወቅ በቢሾፍቱ የተከሰከሰው የአውሮፕላን አደጋ ነው፡፡

የድርጊቱን መነሻና መድረሻ በማሰላሰል የተለያዩ አለም አቀፍ  የዘርፍ ሙያተኞችና ማህበረሰቦች ሃዘናቸውን በመግለፅ ጭምር አየር መንገዳችን ከዚህ በፊት ያከናወናቸውን መልካም ተግባራቶች በማስታወስ ስራዎቹን እያወሱ ይገኛሉ፡፡

የተለያዩ የአለም አቀፍ ሚዲያዎችም ሰፊ ሽፍን በመስጠት የፊት ገፃቸው በማድረግ ሁኔታው እያውሱና እየተነጋገሩበት ይገኛል፡፡ ቢቢሲን ስንመለከት የቢዝነስ ዘጋቢው ሮብ ያንግ ባወጣው ፁህፍ እንዲህ ሲል ሰፊ ሽፋን በመስጠት ያትታል፡፡

 መጀመሪያ ግን ስለ ቦይንግ 737 ማክስ 8 እና አምራች ኩባንያው ምን ያህል እውቀት ይኖረን ይሆን? በማለት ይጠይቃል፡፡

ሪፖርተሩ ቀጥሎ ሲናገርም የመጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ/ም አሳዛኙና አስከፊው  የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፐላን አደጋ በ5 ወራት ውስጥ ቦይንግ ኩባንያ የአውሮፕላን ስሪት ላይ የደረሰውን ሌላ አደጋ በማስታወስ የሃሳቡ ማጠናከሪ ያደርጋል፡፡

ቦይንግ 737 ማክስ 8 በፈረንጆቹ 2017 ወደ ንግድ አገልግሎት ከመጀመራቸው አንስቶ ገና በ2 አመታት እንኳን ያልተቆጠረ ሰለመሆኑም ወደ ኋላ መለስ በማለት ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡

ከ5 ወራት በፊት በወርሃ ጥቅምት የኢንዶኔዢያ መዲና ከሆነችው ጃካርታ ከተነሳ ብዙም ሳይቆይ ተከስክሶ በውስጡ ለነበሩት የ189 ተሳፋሪዎች ህልፈት ምክኒያት የሆነው ላየን ኤር ቦይንግ 737 ማክስ 8 መሆኑ ደግሞ በአውሮፕላኖቹ ላይ ጥያቄ እንዲያነሳ  አድርጎታል፡፡

አውሮፕላኑ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በ3 ወራት ነበር ነገሮች ሁሉ እንዳልነበረ የሆኑት ይላል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ-302ትም ቢሆን ከአምራች ኩባንያው ወጥቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ገና ባለፈው ጥቅምት ስለመሆኑ ይታውሳል፡፡

መቀመጫውን ጃካርታ ያደረገው የበረራ ሙያተኛና የዘርፍ ተንታኝ የሆኑት ጌሪ ስዌጅ ማን በሰዓቱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች ከዊንግስ አውሮፕላን በተሻለ የኢንጅን ስሪት የሚታወቁ ቢሆኑም ቀደምት የኩባንያው ምርቶች ግን አስቸጋሪ የአውሮፕላን ሚዛን አጠባበቅ ችግር እንዳለባቸው ለማየት ይሞክራል፡፡ 

የኢንዶኖዥያው የትራንስፖርቴሽን ደህንነት ኮሚቴ እንደገለፀውም ላየን ኤር ፍላይት 610 አደጋ ከመከሰቱ አስቀድሞ ለፓይለቶች የማንቂያ ምልክት ያሳይ እንደነበር ነው የሚሳዩት፡፡

የሆነው ሆኖ እስካሁን የኢንዶኖዢያው ላየን ኤርም ሆነ የኢትዩጵያ አየር መንገድ ላይ የደረሰውን አደጋ ትክክለኛ ምክኒያት ለመለየት ጊዜው ገና ቢሆንም  ለማንቂያነት የሚያገለግሉ በአውሮፕላኑ የተገጠሙት ሴንሰሮች ከዚህ ቀደም አገልግሎት ሲሰጡ ከነበሩ አውሮፕላኖች ያንሳል በማለት ሃሳቡን አቅርቧል፡፡

የጃካርታው ላየን ኤር ከተከሰከሰ ከቀናት በኋላ የአውሮፕላኑ አምራች ኩባንያ ቦይንግ በአየር መንገዱ ጥናት በማካሄድ በአሜሪካ Avation Angle of Attac ስለተባለችው ሴንሰር በቂ ግንዛቤ ተሰጥተው እንደነበርም ለቢቢሲ ያስረዳሉ፡፡

የአሜሪካው አቬሽን ባለስልጣን በወቅቱ አጥብቆ ማሳሰቡን በማስታወስ የአቬሽን ምንጮች እንደሚሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፓይለቶች በዚህ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ መውሰዳቸውን ጭምር ያብራራል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያጋጠመው የቴክኒክ ክፍተትም ላየን ኤርን  አጋጥሞት የነበረው አይነት ችግር ስለመሆኑም የችግሩን ተመሳሳይነት ለማንሳት ሞክሯል፡፡

የአቬሽን ዱዳዮች ተንዳኝ የሆኑት ጆን ስቲክላንድ ለቢቢሲ እንዳሉትም አደጋው የደረሰበት የኢትዮጵያ አውሮፕላንና የኢንዶኖዢያው ላየን ኤር አዲስና ብዙ ምርመራ የሚጠይቅ በመሆኑ ስለጉዳዩ በጥልቀት ለማውራት ጊዜ አሁን ስላለመሆኑ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

እንደ አጠቃላይ ችግሩ ያሳሰባቸው በርካታ የአለም ሃገራት ደግሞ አደጋው ባጋጠመው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች ተመሳሳይ ስሪት ላይ ያሉ አውሮፕላኖችን ለጊዜውም ቢሆን ከአገልግሎት አግደዋል፡፡  

ቻይናን ጨምሮ እንዶኖቪያም እነዚህን መሰል አውሮፕላኖች ጉዳዩ በጥልቀት እስኪጣራ ድረስ ለጊዜውም ቢሆን በረራውን እንደገቱ በውሳኔቸው አሳውቀዋል፡፡

የሃገራችን አየር መንገድም የቦይንግ ኩባንያ ምርቶች የሆኑ የመጨረሻ ስሪት አውሮፕላኖች 5 ሲኖሩት አንዱ መነሻውን አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አድርጎ ወደ ኬኒያ ናይሮቢ ሲያቀና መጋቢት 1/2011 ዓ/ም ቢሾፍቱ ላይ የተከሰከሰው ነው፡፡

ከዚህ ሁኔታ በነሳትም የኢትዩጵያ አየር መንገድ ቀሪ 4 ተመሳሳይ ስሪት ያላቸውን የቦይንግ 737 አውሮፕላን ምርቶችን ላለመጠቀም መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ይህንን ተከትሎም የቦይንግ አወሮፕላን አምራች ኩባንያ በሰጠው ሃሳብ ዘርፍ ብዙ አገልግሎት የሚሰጠውን የሃገራችን አየር መንገድ በማኛውም የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ሲል ተናግሯል፡፡

በዚህ ሂደት ግን መሰል እና በዘርፍ የተሰማሩ አምራች ኩባንያዎች መሰረታዊ የሆነ ለውጥ እንዲያመጡ  እንደነዚህ አይነት አደጋዎች እንዳይከሰቱና መሰል ጥያቄዎች ጭምር እንዳይነሱ ማድረግ ይጠይቃል ምክኒያቱን ምንም እንኳን የአደጋ ትንሽ ሊኖረው ባይችልም አደጋውን የከፋ የሚያደርገው “የአውሮፕላን አደጋ ያው የአውሮፕላን አደጋ መሆኑ ነው”አበቃሁ፡፡       

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም