ወጣቶች ከጥላቻ ንግግሮችና ከዘረኝነት በመቆጠብ ለአገራቸው ልማት እንዲተጉ ጥሪ ቀረበ

47

አዲስ አበባ የካቲት 7/2011 ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ ከሚተላለፉ የጥላቻ ንግግሮችና ከዘረኝነት በመቆጠብ ለአገራቸው ልማት እንዲተጉ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጥሪ አቀረቡ።

ኢትዮጵያዊያኑ በአገሪቱ እየታየ ያለውን ለውጥ ለማስቀጠል የድርሻቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት በኖርዌይ የኢትዮጵያ ዜጎች በአሁኑ ወቅት በተለይም በማህበራዊ ድረ-ገፆች የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችና የሀሰት ዜናዎች መበራከታቸውን አንስተዋል።

ይህም አገርን ከመገንባት ይልቅ ዘረኝነትን የሚያስፋፋና ለረጅም ዘመናት በሰላምና በመተባበር የኖረን ህዝብ በማጋጨት አገሪቱን ወደማይፈለግ አቅጣጫ የሚያመጣ መሆኑን ነው የተናገሩት።

ወጣቶች ከእንዲህ ያለ ተግባር በመቆጠብ ለአገራቸው ልማት መትጋት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ወይዘሮ ራሄል አክሊሉ እንደተናገሩት በሚኖሩበት አገር ከየት መጡ የሚል ነገር እንደሌለ አገር ቤት ደግሞ እንደዚህ ነው የዚህ ብሄር ነው ሲባል መስማት በጣም ያሳዝናል ብለዋል፡፡

አሁን ያለው ትውልድ  በራሱና  በማንነቱ በመኩራት አ አገሩን ኢትዮጵያን መገንባት እንደለበት ተናግረዋል ፡፡

ወጣት ኑሃሚን አስራት በፌስቡክ በኢንስታግራም ብዙ መለቀቅ የማይገባቸው ነገሮች ሲለቀቁ ይታያል ይህ አግባብ አይደለም እድሉ ስላለ ብቻ አግባብ ያልሆኑ ነገሮች መናገር መጻፍ አግባብ አይደለም ብላለች፡፡

እድሉ ስላለን ብቻ መናገር ሳይሆን  የምናደርገውን ነገር በሃላፊነት ብናደርግ እንደሚገባ ሶሻል ሚዲያንም በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብላለች

የኢትዮጵያ እናቶች ከአርባ ዓመት በላይ በርካታ ትውልድ ገብረዋል በፖለቲከኞች ጦስ የሚገድላቸው መንግሰት ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚ ደርጅቶችም ይገድሏቸዋል።ያስገድሏቸዋልም።ይሄ ነገር መቅረት አለበት የሚሉት ደግሞ ወይዘሮ ሰዋሰው ስልሺ ናቸው ፡፡

 መንግስትም ተቃዋሚ ነን የሚሉ ወይም ተፎካካሪ ነን የሚሉ አክቲቪስቶችም የጥላቻ ንግግር በማድረግ ትውልዱን የበለጠ የሚያጣላና ትውልዱ የሚያጨነግፍ ስራ እንዳይሰሩ አሁንም ለኢትዮጵያ መንግስት በተለይ እነዚህን ሰዎች ገደብ በማስያዝ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ እየታየ ያለውን ለውጥ ያደነቁ ሲሆን ለውጡን ለማስቀጠል የድርሻቸውን እንደሚወጡም ነው አስተያየት ሰጪዎቹ ያረጋገጡት።

በውጭ ያለን ኢትዮያዊያንም አገራችንን እንናፍቃለን ልንረዳ የምንችለውን ያህል እንደአቅማችን እንሞክራለን ያሉትወይዘሮ ሰዋሰው ስለሺ ናቸው

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም