በደብረ በማርቆስ ለፓራ ኦሎምፒክ ገቢ ማሰባሰቢያ ንግድና ባዛር ተከፈተ

65

ደብረማርቆስ መጋቢት 4 / 2011 ፓራ ኦሎፒክ ስፖርትን ለመደገፍ ዓላማ ያደረገ ንግድና ባዛር ዛሬ በደብረ ማርቆስ ከተማ ተከፈተ፡፡

የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን የፓራ ኦሎምፒክ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነቢዩ መኮንን ለኢዜአ እንደተናገሩት የፓራ ኦሎምፒክ ስፖርትን በማጠናከር ራሱን ችሎ እንዲቆም እየተደረገ ነው።

ለዚህም የስፖርት ዘርፉን ለማጠናከር የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር መዘጋጀቱን አመልክተዋል።

አካል ጉዳተኞች ድጋፍ ካገኙ በሁሉም ዘርፎች ውጤታማ እንደሚሆኑ የሚያመለክቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶች እንደሚተላለፉ አስረድተዋል።

በክልሉ መንግሥትና ጃክሮስ በተሰኘ ማስታወቂያ ድርጅት ትብብር በተሰናዳው ዝግጅት "ከሚሰበሰበው ገቢ 75 በመቶ ለስፖርት ዘርፉ ማጠናከሪያ ይውላል" ብለዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ እስከ መጋቢት 12 ቀን 2011 በሚቆየው ዝግጅት ከ 90 በላይ የንግድ ድርጅቶች ይሳተፋሉ።

ከአዲስ አበባ የመጣችውና በአልባሳት ንግድ ሥራ የተሰማራችው ወጣት እጸገነት ተስፋዬ "የዝግጅቱ ዓላማ አስፈላጊና ጠቃሚ በመሆኑ በመሳተፌ የመንፈስ እርካታ ፈጥሮልኛል"ብላለች።

አቶ ዮሐንስ ዓለሙ  የተባሉ ተሳታፊ በበኩላቸው ዝግጅቱi ለአካል ጉዳተኞች የተሰጠውን ትኩረት ማሳያ በመሆኑ በመሳተፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም