ኢዴፓ ከሌሎች አቻ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውህደት ሊፈጥር ነው

90

አዲስ አበባ መጋቢት 4/2011 የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ከሰማያዊ ፓርቲ፣ ከአርበኞች ግንቦት 7 ፣ ለአንድነትና ለፍትህ ንቅናቄና መሰል ፓርቲዎች ጋር ለመዋሃድ ውሳኔ አሳለፈ።

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ሁለተኛ ልዩ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ከመላው አገሪቱ የተውጣጡ አባላት ጋር አካሂዶ ውሳኔና አቅጣጫ አስቀምጧል።

ፓርቲው በጉባኤው  ከፓርቲዎች ጋር ለመዋሀድ ያቀረበውን ሃሳብ አባላቱ በሙሉ ድምጽ መቀበላቸውን  ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ከጉባኤው በኋላ ፓርቲው ከሰማያዊ፣ ከአርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ለፍትህ ንቅናቄ፣ ከመኢዴፓና ሌሎች ፍላጎቱ ካላቸው ፓርቲዎች በጋራ እንደሚሰራ አረጋግጧል።

የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በጉዳዩ ላይ በቂ ውይይት በማድረግ ያስቀመጧቸው ተግባራቶች እንዲጠናቀቁ ውህደቱን እንዲያስፈጽም የጉባኤውን ሙሉ ውክልና ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሃላፊነት መስጠቱም በመግለጫው ተመልክቷል።

ፓርቲው ሲጠቀምበት የነበረው ''ኢዴፓ'' የሚለው ስያሜ፣አርማውና ሌጋሲዎቹ  ከውህደቱ በኋላ ለሌላ ሳይተላለፉ ለታሪክ ቋሚ ቅርሶች ሆነው ይቀመጣሉ ብሏል በመግለጫው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም