ምክር ቤቱ በኢትዮጵያና በሌሎች አገሮች መካከል የተፈረሙ ስምምነቶችን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ

68

አዲስ አበባ መጋቢት 3/2011 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያና በሌሎች አገሮች መካከል የተፈረሙ ስምምነቶችን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ መራ።

ምክር ቤቱ 26ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።    

ለዝርዝር እይታ ከተመሩት አጀንዳዎች መካከል የኢትዮጵያ መንግሥት ከጂቡቱ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር ያደረገው የንግድ ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅ አንዱ ነው።  

በምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት የስምምነቱን ይዘት ሲያቀርቡ እንዳሉት፤ ስምምነቱ የሁለቱን አገሮች የንግድ ግንኙነት በማሳለጥ ተጠቃሚነታቸውን ከፍ የሚያደርግ ነው። 

በአገሮቹ መካከል ያለውን የአሰራር ስርዓት በመጠቀም የትምህርት ዕድሎች፣ የንግድ አውደ ርዕይ፣ ሴሚናሮች፣ አውደ ጥናቶችና ትስስሩን የሚያጠናክሩ የተለያዩ መርሃ ግብሮችን ያካተተ መሆኑን ነው ሚኒስትር ደኤታው ያብራሩት።  

በንግድ ግንኙነቱ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ኮሚቴ ማቋቋም፣ የባለሙያ የልምድ ልውውጥ ማድረግና ጉብኝት የመሳሳሉ በስምምነቱ ውስጥ ተካተዋል።  

ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን በዋናነት ለውጭ ግንኙነትና ሠላም ጉዳዮች በተባባሪነት ደግሞ ለንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መርቷል።      

በኢትዮጵያ መንግሥትና በአውሮፓ የኢንቨስትመንት ባንክ መካከል ለሴቶች ንግድ ሥራ ፈጠራ ብቃት ማሳደጊያ መርሃ ግብር ማስፈጸሚያ የተፈረመውን የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ማጽደቅ የምክር ቤቱ ሌላው አጀንዳ ነበር። 

ሚኒስትር ደኤታው አምባሳደር መስፍን ረቂቅ አዋጁን ዝርዝር ሲያቀርቡ እንደገለጹት፤ የብድሩ መጠን 30 ሚሊዮን ዩሮ ሲሆን በስምንት ከተሞች የሚተገበርና መንግሥት ለሴቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ የያዛቸውን ጥረቶች ለመደገፍ የሚውል ነው። 

አምባሳደሩ እንደሚገልጹት፤ ብድሩ በ18 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው።   

የምክር ቤቱ አባላት ''ከተሞቹ የተመረጡበት መስፈርት በግልጽ አልተቀመጠም፣ የፍትሃዊነት ጉዳይ ሊታሰብበት ይገባል እንዲሁም ከክልሎች ጋር ያለው የቅንጅት አሰራር ምን ያህል ታሳቢ ተደርጓል'' የሚሉ አስተያየቶች አንስተዋል።

ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ከመረመረ በኋላ ለዝርዝር ዕይታ ለገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል። 

በተመሳሳይም በኢትዮጵያ መንግሥትና በጣሊያን ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል ለአነስተኛና መካከለኛ ከተሞች ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያና ማሻሻያ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የተደረገን የ17 ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ ማጽደቂያ ለገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ በአብላጫ ድምጽ ተመርቷል።   በኢትዮጵያና በጣልያን መካከል ለዘላቂና አካታች የግብርና እሴት ሰንሰለት እድገት መርሃ ግብር ማስፈጸሚያ ከጣልያን መንግሥት ጋር የተደረገው የብድር ስምምነትም ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም