ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለይፋዊ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ

695

መጋቢት 3/2011 የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ::

ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽ እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ፕሬዚዳንት ማክሮን በዓለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገበውን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እንደሚጎበኙም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት  በመረጃው ጠቅሷል።