በታች አርማጭሆ ወረዳ 19 ካርቶን የኮንትሮባንድ ሽቶ ተያዘ

92

ጎንደር መጋቢት 2/2011 በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታችአርማጭሆ ወረዳ  ንብረትነቱ የመከላከያ ሰራዊት በሆነ ተሸከርካሪ ላይ  ተደብቆ  የተጫነ 19 ካርቶን የኮንትሮባንድ ሽቶ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ተወካይ ኢንስፔክተር አበበ ደጀን ለኢዜአ እንደተናገሩት የኮንትሮባንድ እቃው የተያዘው ዛሬ እኩለ ቀን አካባቢ የሰሌዳ ቁጥሩ 09655 በሆነ ኦራል ተሸከርካሪ ላይ ነው፡፡

ከሁመራ ተነስቶ ወደ ጎንደር ያመራ የነበረው ተሸከርካሪ በወረዳው አሸሬ በተባለው ከተማ በሚገኘው የፍተሻ ኬላ እንዲቆም ሲጠየቅ ኬላ በመጣስ ለማለፍ መሞከሩን ኢንስፔክተሩ አመልክተዋል፡፡

ፖሊስና የአካባቢው የፀጥታ ኃይል በጋራ ሆነው ባደረጉት ክትትል አሽከርካሪው  የጫነውን የኮንትሮባንድ ሽቶ ጫካ ውስጥ አራግፎ ለማምለጥ ሲሞክር በጥይት ቆስሎ መያዙን አስታውቀዋል፡፡

አሽከርካሪው በአሁኑ ወቅት ለህክምና እርዳታ ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል መላኩን የጠቆሙት ኢንስፔክተሩ የኮንትሮባንድ እቃው በፖሊስ እጅ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡    

የተያዘው የኮንትሮባንድ ሽቶ በቁጥር 1ሺ 882 መሆኑንና  ግምቱም 200ሺ ብር እንደሚጠጋ  ኢንስፔክተር አበበ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም