ሸክ መሃመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በአውሮፕላን በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ

76

አዲስ አበባ መጋቢት 2/2011 የሚድሮክ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሊቀመንበር ሸህ መሃመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ።

ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር በነበረው የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላን መከሰከሱን ተከትሎ  መንገደኞችና የበረራ ሰራተኞች ሕይወት ማለፉ ይታወቃል።

ሸክ መሃመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ ዛሬ ለኢዜአ  በላኩት መግለጫ ለተጎጂ ቤተሰቦች፣ ለአየር መንገዱ ሰራተኞችና ማኔጅመንት አባላት አንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያዊያን መጽናናትን ተመኝተዋል።

አደጋ የደረሰበት ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ኢትዮጵያን ጨምሮ የ35 አገራት ዜጎችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በመብረር ላይ ሳለ  መከስከሱ ይታወቃል።

በአደጋውም የ157 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

የአደጋውን መንስኤ ለማወቅም የአውሮፕላኑ የመረጃ ሳጥን በመገኘቱ በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም