በናጎያ የሴቶች ማራቶን ሂሊያ ጁሃንስ ስታሸንፍ መሰረት ደፋር አራተኛ ሆና አጠናቃለች

90

መጋቢት 2/2011 ናሚቢያዊቷ የረጅም ርቀት ሯጭ ሂሊያ ጁሀንስ በጃፓን በናጎያ የሴቶች ማራቶን አሸናፊ ሆናለች፡፡

በውድድሩ መሰረት ደፋር አራተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡

የኮሜን ዌልዝ ሻምፒዮና ሂሊያ ጁሃንስ በዚሁ በዓለማቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ውድድር ሁለት ሰዓት ከሃያ ሁለት ደቂቃ ከሃያ አምስት ሰከንድ በመግባት ነው አሸናፊ የሆነችው፡፡

በዚሁ የሴቶች ማራቶን ኬኒያዊቷ ቪሲሊን ጆፕክሰን ሁለተኛ ስትወጣ ሌላዋ ኬኒያዊት ቫሌሪ ጀሚል ሶስተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡

ቪሲሊን ሁለተኛ የወጣችው  2 ሰዓት ከ22 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በማስመዝገብ ሲሆን  ሌላዋ ኪኒያዊት ቫሌሪ ጀሚል   2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ01 ሰከንድ በመግባት ነው፡፡

ኢትዮጵያዊቷ መሰረት ደፋር 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ33 ሰከንድ በመግባት አራተኛ ሆና ማጠናቀቋን የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በድረገጹ አስነብቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም